የጉመር ወረዳ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት 43ኛ መደበኛ ጉባኤ የወረዳው የ2017 ዓ.ም በጀት 297,134,270 ብር አጽድቋል።

የጉመር ወረዳ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት 43ኛ መደበኛ ጉባኤ የወረዳው የ2017 ዓ.ም በጀት 297,134,270 ብር አጽድቋል።

ም/ቤቱ ባካሄደው ጉባኤ የወረዳው ም/ቤት የ2016 ማጠቃለያ ሪፖርትና የ2017 እቅድ እንዲሁም የወረዳው አስተዳደር ም/ቤት የ2016 ማጠቃለያ ሪፖርትና የ2017 እቅድ ላይ ሰፊ ውይይቶች ተደርጎ ፀድቀዋል፡፡

የጉመር ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ትዛዙ ጭቅስየ በጉባኤው በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት በወረዳ የታቀዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶች በአግባቡ ተፈጻሚ በማድረግ የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የአስፈጻሚ አካላት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

በምክር ቤት አባል በተለያዩ ጊዜይነሱ የነበሩ የልማትና የመልከም አስተዳደር ጥያቄዎች ምክር ቤቱም እስከ ቀበሌ በመውረድ የተከናወኑ ተግባራት በመስክ ምልከታ ለማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል ።

የጉመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ከድር የ2016 በጀት ዓመት የሴክተር መስሪያ ቤቶች እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በግብርናው ዘርፍ በ2015/16 ምርት ዘመን በመኸር በዋና ዋና ሰብሎች 5,933 ሄክታር ለማልማት ታቅዶ 5,992 ሄ/ር ማልማት ተችሏል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በበጋ ስንዴ መስኖ ልማት 110 ሄ/ር ለማልማት ታቀዶ 110 ሄክታር መሬት በመስኖ ለምቷል ።
በአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ 5,556 ሄ/ር መሬት በንኡስ ተፋሰሶች ለማልማት ታቅዶ 5,649.5 ተፈጻሚ ሆኗል ብለዋል ። የእንስሳት ዝርያ ለማሻሻል በአራት ክለስተሮች በተሰራው ከፍተኛ ስራ በሲንክሮናይዜሽን ፣ በመደበኛ ማዳቀል እና በተሻሻለ ኮርማ 3,855 ላሞች ማዳቀል መቻሉን አቅርበዋል።

በገጠርና በከተማ 2,332 ስራ አጥ ወጣቶች በተለያዩ የስራ መስኮች እንዲሰማሩ በማድረግ ለእነዚህ ተደራጅተው ለሚሰሩ ወጣቶቾ 6,075,000 ብር ብድር ማሰራጨት መቻሉን በሪፖርቱ አመላክተዋል።

በ2016 የትምህርት ዘመን የመደበኛ ተማሪዎች ከ1እስከ12ኛ ክፍል11,989 ተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተማር ታቅዶ የእቅዱ 79.71% ተፈፃሚ ሆኗል

በጤናው ዘርፍ ለ3,351 እናቶች በሰለጠነ ባለሙያ በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ ለ2,653 እናቶች በሰለጠኑ የጤና ባለሙያ አገልግሎት ማግኘት ችሏል።

የገቢ አሰባሰብ ለማሳደግ በዓመቱ 90, 388,090 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 87,047,328..59 ብር ማሳከት ተችለዋል ያሉት ዋና አስተዳደር በህብረተሰብ ተሳትፎና በመንግስት ድጋፍ በተለያዩ ቀበሌዎች ከፍተኛ የመንገድ ልማት ስራዎች መሰራት መቻሉን ተናግረዋል።

ከምክር ቤቱ አባላትም የመብራት መቆራረጥ፣ ከፍተኛ የሌብነት ወንጀል ፣ የጤና ተቋማት የመድሀኒት እጥረት፣ የትምህርት ጥራት ችግር የትራንስፖርት የታሪፍ ችግር የሚሉ በስፋት የተነሱ ሲሆን በሚመለከታቸው የሴክተር መስሪያ ቤት ሀላፊዎችም ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመድረኩ የ2016 ዓ.ም በ2016 በጀት አመት የጉመር ወረዳ ፍ /ቤት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በአጠቃላይ በምክር ቤቱ አባላት እና ከቋሚ ኮምቴዎች አስተያየቶች ቀርቦ ከፍርድ ቤት ዳኛ ማብራርያና ምላሽ ሰጥተዋል።

በጉባኤውሹመቶች መርምሮ ያፀቀ ሲሆን በዚህም
1,አቶ ሲሳይ ስፍር ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ ፣
2 , አቶ አቶ አልዩ ናስር የመንግስት ኮምዩኒኬሽ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ ፣
3, ዶ/ር ኢማሙዲን አግዛ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ /ቤት ሀላፊ በመሆን እንዲያገለግሉ የቀረቡ ዕጩዎች በምክርቤቱ አባሉ በሙሉ ድምፅ ፀድቋልሲል የዘገበው የጉመር ወረዳመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነወ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *