የጆካ ባህላዊ አስተዳደር ሸንጎ የተወሰኑ ህጎችን አሻሻለ።

ዛሬ በጉራጌ ዞን በእምድብር ከተማ ውስጥ በሚገኘው የጉራጌ ባህላዊ ሸንጎ ፅ/ቤት ቅጥር ግቢ በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ሸንጎው የተወሰኑ ህጎችን ማሻሻሉ የጆካ ባህላዊ አስተዳደር ሸንጎ ፀሃፊ የሆኑት ዳሞ በለጠ ወልዴ ገልፀዋል።

እንደ እሳቸው ገለፃ ዛሬ በምለአተ ጉባኤ የፀደቁት (ቂጫ) ህጎች በመጀመሪያ በጆካ ባህላዊ አስተዳደር ሸንጎ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተተቹና 95ቱ የምክር ቤት አባላት የተግባቡባቸው መሆኑን ጠቁመዋል።

በዛሬው እለት በምለአተ ጉባኤ ተሻሽለው የፀደቁት (ቂጫ) ህጎች ሆን ብሎ የሰውን ህይወት ማጥፋት (ሙራ ደም)፤በስህተት የሰውን ህይወት ማጥፋት (መዳራ) ፣የመዳራ መዳራ፣የጋብቻና የለቅሶ ስነስርዓት መስተንግዶ መሆናቸው ገልፀዋል።

ሆን ብሎና አስቦበት ግፍ በመፈፀም የሰውን ህይወት ማጥፋት ከዚህ ቀደም 2 መቶ ሺ ብር የነበረ ሲሆን በተሻሻለው ቂጫ 3 መቶ ሺህ ብር ሲሆን መዳራ ወይንም በአጋጣሚ ወይንም በስህተት የሰውን ህይወት ያጠፋ መቀጮው መቶ ሺህ የነበረው 150 ሺህ ብር ሲሆን የመዳራ መዳራ ደግሞ 37 ሺህ 5 መቶ ብር የነበረው መቶ ሺህ ብር በማድረግ ተሻሽለዋል።

በሸንጎው ማሻሸያ ጋብቻ (ቸግ) በሚፈፀምበት ወቅት በወንዱም ሆነ በሴቷ ቤት በሬ ወይንም ወይፈን ማረድ እንዲቀርና በጠቦት በግ መስተናገድ እንዳለበት ህጉ ለምለዓተ ጉባኤው ቀርቦ ሲፀድቅ ሴቷ ቤት የሚላኩት ሽማግሌዎች ቁጥር እስከ 7 እንዲሆንና የሰርገኛ ቁጥር እስከ 10 እንዲሆንም ተወስኗል።

በሬ ወይንም ወይፈን አርዶ እንግዳ(ሰርገኛ) የተቀበለ ቅጣት የተጣለ ሲሆን ይህም የወንዱም ሆነ የሴቷ ቤተሰብ 25 ሺህ ብር እንደሚከፍል ሸንጎው ወስነዋል።

እንደ ባህል ሸንጎ ፀሃፊው አክለውም እነኚህ ህጎች ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት በተለይ የመኪና አደጋ መብዛትና የጥንቃቄ ጉድለት በመታየቱ ሲሆን የጋብቻና የለቅሶ ስነ-ስረዓት መስተንግዶ በተመለከተ ደግሞ ያላስፈላጊ ወጪ እየወጣ በመሆኑና በዚህ ወጪ ምክንያት ፍቺ በመበራከቱ ፣ከእርስት መፈናቀል እና መሰል ችግሮች ማህበረሰቡ ላይ በመደቀኑ ነው ብለዋል።

የጆካ ባህላዊ አስተዳደር ሸንጎ በዛሬው ጉባኤ እነኚህ እና መሰል የባህላዊ አስተዳደር ህጎች (ቂጫ) ላይ በመምከር ለሰኔ 18/2014 ዓ.ም.ቀጠሮ በመጣል የጉባኤው ፍፃሜ ሆኗል ሲል መረጃው ያደረሰን የእምድብር ከተማ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *