የደቡብ ክልል የብልጽግና አመራሮች በጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ በሞዴል አርሶ አደሮች የለሙ የአቮካዶ ፍራፍሬ ማሳዎች ሌሎች የግብርና ስራዎች እየጎበኙ ይገኛሉ።

ለ4 ተከታታይ ቀናት በክላስተር የሚሰጠው የደቡብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የአመራሮች ስልጠና በቡታጅራ ከተማ እየተሰጠ እንደሆነ ይታወሳል።

በመሆኑም ከዚህ ስልጠና ጎን ለጎን የደቡብ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ የአቮካዶ ፍራፍሬ ማሳዎች እየጎበኙ ይገኛሉ።

የደቡብ ክልል ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት እንዳሉት መንግስት የ10 አመት መሪ እቅድ በማቀድ የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግና የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ይገኛል።

አሁን የተጀመሩው 30-40-30 የፍራፍሬ ምርት ከምግብ ፍጆታ በተጨማሪ የአርሶ አደሩ ኢኮኖሚ ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል ገልጸዋል ።

በጉብኝቱ የደቡብ ክልል ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል፣ የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክፍሌ ለማ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ከክልሉ ከተለያየ ቦታ የመጡ የዞን አመራሮች ተሳትፈዋል ።
በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *