የደቡብ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በሺንሺቾ እና ቡኢ ከተሞች በባስኬት ፈንድ ለሚያስገነባቸው የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች የግንባታ ስምምነት ፊርማ ስነሥርዓት ከሁለት ውሃ ሥራ ተቋራጮች ጋር ፈፅሟል፡፡

በስምምነት ፊርማ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ እንደገለጹት የክልሉን ህዝብ የመጠጥ ውሃ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከመንግስትም ሆነ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የሚገኘውን ሀብት በአግባቡ በመጠቀምቢሮው በ2013 በጀት ዓመት 178 የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማትን በማስገንባትና በማጠናቀቅ ከ397 ሺህ በላይ የክልሉን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ከማድረጉ በላይ፣ የክልሉን መጠጥ ውሃ ሽፋን ከነበረበት 40.6 በመቶ ወደ 46 በመቶ ማሰደግ እንደቻለ ጠቁመዋል።

አሁን ምየክልሉ ሕብረተሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ያልተመለሰ በመሆኑ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡የምላሹ አካል የሆነው በካምባታ ጠምባሮ ዞን በሺንሺቾ እና በጉራጌ ዞን ቡኢ ከተሞች የሚገነቡት የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች የጥናት ሥራው ተጠናቅቆ የግንባታ ሥራ ለማስጀመር በቂ ዝግጅት እንደተደረገ፤ሁለቱም ፕሮጀክቶች ከ204 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት እንደተያዘላቸውና ግንባታቸውም በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቁ ሀላፊው ገልጸዋል።

ፕሮጀክቶቹ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቁ በሁለቱም ከተሞች ከ80 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉና የሁለቱንም ከተሞች የመጠጥ ውሃ ተዳራሽነት ከፍ ከማድረጉም በላይ የክልሉንም የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን እንደሚያሳድግ ገልጸዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ጀማል በበኩላቸው የቡኢ ከተማ እጅግ በጣም የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር እንደለበት አስረድተው የዞኑ መንግስት የህብረተሰቡ የንፁህ የመጠጥ ውሃ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ፕሮጀክቱን በቦታው ተገኝቶ ክትትል ከማድረግ አንስቶ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ እንደሚደረግና በተያዘላት ጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በቅርበት እንደሚሠራ ያለውን ቁርጠኝነት መግለፃቸው ከክልሉ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

= አካባቢህን ጠብቅ!
= ወደ ግንባር ዝመት!
= መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *