የዞኑ የልማት ፕሮጀክቶች ውጤታማ እንዲሁኑና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድግ ሴክተሮች በእቅድ እንዲመሩ ለማስቻልና በተግባራት አፈጻጸም እረገድ የግልጸኝነትና ተጠያቂነት አሰራር ይበልጥ እንዲሰፍን በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ፕላን መምሪያ አስታወቀ።

የህዝቅ ቁጥር እድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን እና ፍትሀዊ የበጀት ክፍፍል እንዲኖር በትኩረት እየሰራ እንደሆነ መምሪያው አስታውቋል።

መምሪያው በ2013 አመተ ምህረት የስራ አፈጻጸምና የ2014 አመተ ምህረት እቅድ ዝግጅት እና አመታዊ የምክክር ጉባኤውን ዛሬ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል ።

የጉራጌ ዞን ፕላን መምሪያ ኃላፊ አቶ ከበደ ኃይሌ በምክክር መድረክ ላይ እንደገለጹት ነባርና በአዲስ በእቅድ የተያዙ የካፒታል ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ጥራቱ በጠበቀ መልኩ እንዲጠናቀቁ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የሚስተዋሉ ውስንነቶች ለማረም የሚደረጉ ድጋፍና ክትትሎች ተጠናክረው ተናግረዋል።

የዞኑ የልማት ፕሮጀክቶች ውጤታማ እንዲሁኑና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድግ ሴክተሮች በእቅድ እንዲመሩ ለማስቻልና በተግባራት አፈጻጸም እረገድ የግልጸኝነትና ተጠያቂነት አሰራር ይበልጥ እንዲሰፍን በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ከበደ ኃይሌ ተናግረዋል።

ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲረጋገጥና ዘመናዊ የመረጃ አያያዝና ስርጭት ስርአት በመዘርጋት ረገድ በቀጣይ በትኩረት መሰራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የፕላንና ልማት ተቋም እያንዳንዱ ስራ በመረጃ የተደገፈ በማድረግ እና የቴክኖሎጂ አቅርቦት ማሻሻል ላይ ትኩረት ከተሰጠው በእያንዳንዱ መረጃ ትንተናና በጀት ድልድል ላይ ፍትሃዊነትና ግልጸኝነት እንዲኖር ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል ።

በመሆኑም ተቋሙ አዲስ እንደመሆኑ መጠን በርካታ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ በሰው ሀይል፣ በቁሳቁስ በበጀት፣ በቴክኖሎጂ ሊደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።

እቅድ የሁሉም ነገር መሰረት ነው ያሉት አቶ ከበደ ማህበረሰቡ ካለበት የመሰረተ ልማት ፍላጎት አንጻር መንግስት የሚያቅዳቸው እቅዶችና የካፒታል ፕሮጀክቶች በወቅቱ እንዲጠናቀቁ ክትትሉ ሊጠናከር ይገባል ብለዋል።

የመምርያው የልማት እቅድ ባለሙያ አቶ ኮስትር ጌታቸው የአመቱ እቅድ አፈጻጸም በአቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት እዣ፣ ሙህር አክሊል፣ ሶዶ፣ እነሞር እና ኤነር እና ቡታጅራ ከተማ ጥሩ አፈጻጸም ያላቸው መሆናቸው አመላክተው ሌሎችም መዋቅሮች የተሻለ አፈፃፀም ካላቸው መዋቅሮች ተሞክሮ ሊወስዱ ይገባል ተብለዋል።

አቶ ብርሃኑ ቆንዴ ከሶዶ ወረዳ እና አቶ ደምስ ተክሉ ከእዣ ወረዳ የተገኙ ተሳታፊዎች ሲሆኑ በወረዳቸው ከአመት እቅድ እስከ አስር አመት እቅድ ተፈጻሚ እንዲሆኑ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸው አሳውቀዋል።

የሚመደበው በጀት ከወረዳው ህዝብ ቁጥር ተመጣጣኝ እንዲሆን ከአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማነጻጸር የስነ-ህዝብ ስራው አጠናክረው እየሰሩ እንደነበር ተናግረዋል ።

አክለውም በቀጣይም የሚሰሩ የካፒታል ፕሮጀክቶች በጊዜው እንዲጠናቀቁ እና ጥራታቸው የተጠበቀ ሆኖ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ክትትላቸው አጠናክረው እእንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በጉባኤው የመምሪያው ኃላፊ እና የማኔጅመንት አካላት የወረዳ የጽ/ቤቱ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *