የዞኑ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የህብረተሰቡን የመልማት ፍላጎት ጥያቄ ለመመለስ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ ገለጸ።

መምሪያው የ2014 የግብር ዘመን የግብር መክፈያ ወቅት በማስመልከት ከባለድርሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ መንግስት የህብረተሰቡ የተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የመሰረተ ልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን ታክስ ወሳኝ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ትክክለኛ ገቢ ተሰብስቦ የህዝቡ የመልማት ፍላጎት ደረጃ በደረጃ ማርካት እንዲቻል የገቢ ተቋምና የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ እንደሆነ ገልፀዋል።

በመድረኩ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል ፣የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ አርሺያ አህመድ ጨምሮ የዞን፣ የወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *