የዞኑ አስተዳደር ክለቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆን የሚያደርገውን እገዛ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ገለጸ።

የቸሃ የጆካ እግርኳስ ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ጉራጌ ዞን በመወከል ሻምፒዮና መሆኑን ተከትሎ በሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ ወደ ድሬዳዋ ያቀናል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ እንዳሉት ዞኑ በሁሉም ዘርፎች እምቅ አቅም መኖሩን ተከትሎ በስፖርቱ ዘርፉም ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ይገኛል።

በስፖርቱ ዘርፍ በትኩረት በመስራት የወጣቶችን አቅም በማሳደግ በዞኑ ብሎም በሀገር ደረጃ ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት መስራት ይገባል ብለዋል።

ክለቡ የዞኑ እሴቶችን ከማስተዋወቅ አንጻር ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት አቶ አበራ ክለቡም በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆን የዞኑ አስተዳደር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ለክለቡ የ4መቶ ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ ክለቡ ቀጣይ በሚደረገው ውድድር ውጤታማ የሆነ ስራ በመስራት በሀገር አቀፍ ደረጃ የዞኑ ማህበረሰብ ከፍ ለማድረግ መስራት ይጠበቅባችኃል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን በበኩላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በክልሉ የተሳተፈው የጆካ እግርኳስ ቡድን ሻምፒዮና መሆኑን ተከትሎ በድረዳዋ ለሚደረገው በሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ለመሳተፍ ሽኝት መደረጉንም ገልጸዋል።

ከሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ አቅም ያላቸው ተጫዋቾች ያሳተፈ ክለብ በመሆኑ የማህበረሰቡ ማንነት፣ ቋንቋና ባህል ከማስተዋወቅ ባለፈ በዘርፉ ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የዞኑ አስተዳደር ለወልቂጤ ከነማ እግር ኳስ ክለብ፣ ለዘቢደር አትሌቲክስ ክለብ፣ በዞንና በክልል ደረጃ ለሚደረጉ ውድድሮች በበጀት በመደገፍ ላደረጉት እገዛ አመስግነዋል።

ስፖርት ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የስፖርት ማህበረሰብ ለክለቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

የቸሃ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ሽምንሳ ስፖርት ከውድድር ባለፈ ለሰላም፣ ለወንድማማችና አንድነት በማጠናከር ረገድ ሚናው የላቀ ነው።

ክለቡ በቀጣይ ውድድር ውጤታማ እንዲሆን የሚያደርጉትን እገዛ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረው ለተደረገላቸው የምሳና የሽኝት ፕሮግራምም አመስግነዋል።

ስፖርቱ ህዝባዊ መሰረት ለማስያዝ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መኖሩ ያነሱት አስተዳዳሪው ባለሀብቱ፣ ነጋዴው ማህበረሰብና ሌሎችም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉም አስገንዝበዋል።

የምሳ ግብዣ የተደረገላቸው የጆካ እግርኳስ ቡድን ተጫዋቾች እንዳሉት የዞኑ አስተዳደር ያደረገላቸው የምሳና የሽኝት ፕሮግራም አመስግነዋል።

በቀጣይ በድሬዳዋ ከተማ በሚደረገው በሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮና ላይ ውጤታማ ለመሆን ጠንክረው እንደሚጫወቱ ገልጸዋል።

የቸሃ ወረዳ አስተዳደር ክለቡ በፋይናንስ በመደገፍ ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ ላደረገው አስተዋጽኦ የእውቅናና ሽልማት ተበርክቶለታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *