መምሪያው የ2014 አመት ምህረት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀምና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ።
የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ተመስገን ገ/መድህን በምክክር መድረኩ ወቅት እንደተናገሩት የዞኑ ብሔረሰቦችን ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና ሌሎች እሴቶችን ለማልማትና ለማስተዋወቅ የዞኑ ህዝብ በሚገልፅ መልኩ ይበልጥ ለመጠቀም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
የዞኑ ብሔረሰቦችን ባህል፣ ታሪክና ቅርሶችን በመጠበቅና በማልማት በዩኔስኮ የማስመዝገብ ስራዎችን እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ተመስገን በቀጣይም ሌሎችም ያልተመዘገቡ እሴቶቻችን ለማስመዝገብ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
አክለውም ከቋንቋ አንፃር የቀቤናና የማረቆ ብሔረሰብ ቋንቋዎችን እንደ አንድ የትምህርት አይነት እየተሰጠ መሆኑና ይህም በሁለተኛ ደረጃና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ እንዲሰጥ ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራም ጠቁመዋል።
ከጉራጊኛ ቋንቋ እንፃር በ2006 ዓ.ም የፀደቀ የጉራጊኛ ቋንቋ ፊደል ገበታ ታትሞ በተመረጡ ጣቢያዎች ላይ በሙከራ ደረጃ መጀመሩና ወደ ተግባር መገባቱን የገለፁት ኃላፊው በተወሰነ መልኩ መግባባት ላይ የሚጠይቁ ስራዎች መኖራቸውና በቀጣይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራም ተናግረዋል።
እንደ አቶ ተመስገን ገለፃ የብሔረሰቦቹ ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና ቅርሶችን መረጃ በመያዝ የማልማት፣ የመሰነድና ለኢኮኖሚ የማብቃት ስራዎችን እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው ከዚህ በፊት የተሰነዱ መፅሐፎች ያሉ ሲሆን እነዚህም ለትውልድ ለማስተላለፍ በትኩረት እንደምሰራም ገልፀዋል።
አያይዘውም ባህላዊ እሴቶችን የመጠበቅ፣ የማልማት፣ እንክብካቤ የማድረግ ስራ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ የብሔረሰቦቹ ተወላጆች፣ የባለሀብቶች፣ የባህል ሸንጎ አስተዳዳሪዎች፣ የሀይማኖት ተቋማቶች፣ የወጣቶችና የሌሎችም ባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።
በተለይም የጉራጌ ቋንቋ በማልማት ትውልድ እንዲማርበት ከማድረግ አንፃር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም በመድረኩ ተመላክቷል።
በምክክር መድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎች በጋራ በሰጡት አስተያየት የዞኑ ብሔረሰቦችን ባህል፣ ቋንቋና ታሪክና ሌሎችም እሴቶችን ከማልማትና ከማሳደግ በተጨማሪ በመደጋገፍ ባህሎቻችንን ሳይበረዙ ለትውልድ ለማስተላለፍ በቅንጅት መስራት አለብን ብለዋል።
በብሔረሰቦቹ ውስጥ ያሉትን እምቅ ሀብቶችን ለማጎልበትና በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚጠይቅም አመላክተዋል።
በቀረበው ሪፖርት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ሰነድ በመፈራረም ተጠናቋል።
በመድረኩም ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙሁራን፣ የጉራጌ ልማት ማህበር ተወካይና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ነው።
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx