የዞኑ ማህበረሰብ በመንገድ ልማት ስራ ያለውን የቆየ ልምድ ይበልጥ በመጠቀም በመንገድ ዘርፍ እያደረገው ያለው ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

የካቲ

በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ በዞኑ እየተሰሩ ያሉ የመንገድ ስራዎችን ህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገለጹ።

በዞኑ ጌታ፣ ቸሃ፣ እዣ፣ እኖር እና አበሽጌ ወረዳዎች ላይ በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተሰሩ ያሉ የጠጠር መንገድ ስራዎች የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሙራድ ከድር ጨምሮ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የየወረዳው የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ከድር በመስክ ምልከታው ወቅት እንዳሉት ጉራጌ በመንገድ ልማት ስራ ቀድሞም የመንገድ ጥቅም በተገቢው በመረዳት የጀመረ ማህበረሰብ እንደሆነ ጠቅሰው የቀድሞ አባቶች የጀመሩት የመንገድ ስራ ከማስቀጠል አንጻር ውስንነት እንደነበረና አሁን ላይ ማህበረሰቡ የመንገድ ፋይዳ በተገቢው በመረዳት በርካታ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል።

በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች መንግስትና የህብረተሰብ አቅም በማቀናጀት 130 ኪሎሜትር የአፈር ስራ እየተሰራ ይገኛል ያሉት ኃላፊው በዚህም 90 ኪሎሜትር በጠጠር ዳምፕ ከማድረግ ባለፈ 80ኪሎሜትር የብተና ስራ እየተሰራ ሲሆን በዚህም 158 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉንም ተናግረዋል።

መንገዶቹ መሰራታቸው የዞኑ ማህበረሰብ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚ እንዲሆን ያስችለዋል ያሉት ኃላፊው ማህበረተሰቡ በኢኮኖሚ ከፍተኛ እንቅስቃሴና በንግድ የሚታወቅ ከመሆኑም ባለፈ ያሉትን ትውፊቶችን ለቱሪስት ለማስጎብኘትና በኢንቨስትመንት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ አመላክተዋል።

በመሆኑም ማህበረሰቡ በመንገድ ስራ ያለውን ልምድ ይበልጥ በመጠቀም የጀመሩትን የመንገድ ልማት ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀው መንገድ መስራት ብቻ ሳይሆን እየተሰሩ ያሉ መንገዶች ህብረተሰቡ በተለያየ መልኩ መጠበቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የጌታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በህሩ ኸይረዲን በወረዳው በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ 30 ኪሎ ሜትር መንገድ የሚሰሩ ሲሆን ይህም ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉንም ተናግረዋል።

መንገዶቹ መሰራታቸው ማህበረሰቡ በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ብለዋል።

በወረዳው ያለውን የመንገድ እጦት ችግር ለመቅረፍ የወረዳው ህብረተሰብ አቅም በመጠቀም እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው ይህ ስራ በሁሉም ቀበሌዎች እንዲሰፋ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሆን በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው የጉራጌ ማህበረሰብ ቀድሞውኑ የመንገድ ልማት ድርጅት በማቋቋም በመንገድ ስራ ያላቸውን ተሞክሮ ይበልጥ በመጠቀም በመንገድ ዘርፍ ከመንግስት በመቀናጀት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል።

በወረዳው በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ 50 ኪሎ ሜትር መንገድ እየተሰራ ሲሆን ከነዚህም 30 ኪሎ ሜትር ጥገና እና 20 ኪሎ ሜትር አዲስ ብሎም 3 የድልድይና 3 አነስተኛ ስትራክቸር እየተሰራ እንደሚገኝ ያነሱት አቶ ዘውዱ በዚህም 35 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉንም አመላክተዋል።

የቸሃ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ አድማሱ በወረዳው በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ 10 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር መንገድ በማቀድ እስካሁን ከ22 ኪሎሜትር በላይ መሰራቱን ገልጸው በዚህም 13 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ወጪ መሰራቱንም አስረድተዋል።

የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ተክሌ በወረዳው መንግስት ያልደረሰባቸውና ጊዜ ይወስዱ የነበሩ የመንገድ ልማት ስራ የህብረተሰቡን አቅም በማስተባበርና ከመንግስት ጎን በመሆን 64 ኪሎሜትር መንገድ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በዚህም ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉንና እስካሁን 20 ኪሎሜትር ጠጠር በማንጠፍ ማጠናቀቃቸውን አመላክተዋል።

አርሶ አደሩ አምራች ከመሆኑ አንጻር ያመረተውን ምርት ወደ ገበያ ለማውጣት የመንገድ ችግር እንደነበር ጠቅሰው ይህ መንገድ መሰራቱ የተመረተውን ምርት ለገበያ ከማውጣት ባለፈ አንቡላንስ እንዲገባና በሌሎችም ዘርፎች ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል ብለዋል።

የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አህመድ በወረዳው በጥገናና በአዲስ 55 ኪሎሜትር እየተሰራ እንደሚገኝና በዚህም 19 ሚሊዮን 781 ሺህ ብር በላይ ወጪ መደረጉን ጠቅሰው የወረዳው ማህበረሰብ አምራች በመሆኑ ያመረተውን ምርት ወደ ገበያ እንዲወጣ ከማድረጉም በላይ በሁሉም ዘርፎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።

አቶ ትዛዙ ሸዋርጋ ከጌታ፣ አቶ ፈቀደ ከቸሃ፣ አቶ ይብጌታ ዘብር ከእዣ፣ አቶ ነዱ ግዛ ከእኖር ወረዳዎች ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ናቸው።

እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ ከዚህ በፊት መንገዶቹ ባለመሰራታቸው በወረዳቸው በሁሉም ዘርፎች ተጠቃሚ እየሆኑ እንዳልነበር አንስተው አሁን ላይ መንገዱ በመሰራቱ ሁለንተናዊ ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ገንዘብ በማዋጣት ከመንግስት ጎን በመሆን እየተሰሩ ያሉ መንገዶች በተገቢው እንደሚጠብቁትና እንደሚንከባከቡት መግለጻቸው የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Tiwter https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *