የዞኑ መረጃ ወቅታዊና ጥራት ያለው እንዲሁም በሶፍት ዌር የታገዘ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የጉራጌ ዞን ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በዴቭ ኢንፎ፣በጂአይኤስ እንዲሁም በመረጃ አያያዝና አተገባበር ዙሪያ ከወረዳ፣ ከከተማ አስተዳደሮችና ከመምሪያ ለተውጣጡ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ለ4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።

የጉራጌ ዞን ፖላንና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ከበደ ሀይሌ ስልጠናውን ሲያስጀምሩ እንደገለጹት የዞኑ መረጃ ወቅታዊ፣ጥራት ያለው እንዲሁም በሶፍት ዌር የታገዘ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል።

ስልጠናው የሚሰጠው በዴቭ ኢንፎ(በአንድ ቋት የተቀመጡ መረጃዎች በማንኛውም ቦታና ጊዜ የምናገኝበትና (በጂአይኤስ) በአጠቃላይ የሚሰሩ ስራዎች ወደ መረጃ መረብ የማስገባት ስራ ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል።

ወቅቱ ሶፍትዌሮች በየጊዜው እየተሻሻሉ እየመጡ ይገኛሉ ያሉት አቶ ከበደ ኃይሌ በለተይም ባሉ የመሬት ስፋት ፣የጤና፣ የግብርና ተቋማት እንዲሁም የቆዳ ስፋት ታሳቢ በማድረግ የበጀት ቀመር ሰለሚሰራ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ስልጠናው ከተሰጠ በኃላ አትላስ ዴኤቭ ኢንፎና ጂአይኤስ መሰረት ባደረገ መልኩ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ በጊዜና በአግባቡ ሊደርስ በሚችል ሁኔታ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል።

በአሁን ሰአት የወረዳ ካርታዎች እየተሰሩ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ከበደ ቀጣይ የከተሞችና የቀበሌዎች ካርታ በዚህ መረጃ መነሻነት እንደሚሰራ አሳውቀዋል።

አክለውም በዞኑ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦች፣ ታሪካዊ ቦታዎችና ቅርሶች በጂአይኤስ በማስገባት ማንኛውም ሰው በየትኛውም ቦታ መረጃ ለማግኘት ያስችላል።

አቶ ከበደ አያይዘውም ቀጣይ የበጀት ክፍፍልን በፍትሀዊነትና በጥራት ለማከፋፈል ስልጠናው ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ስልጠናው ለ4 ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል መሆኑ ከመምሪያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *