የዞኑ ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መምሪያው በሁሉም ዘርፍ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን በቀጣይም ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ገለጸ።

የዞኑ ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መምሪያው በሁሉም ዘርፍ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን በቀጣይም ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ገለጸ።

የጉራጌ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ የ2016 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም እና የ2017 ዓ.ም እቅድ የግብ ስምምነት ላይ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

በበጀት አመቱ የነበሩ ጠንካራ ተግባራት ይበልጥ በማጠናከርና ጉድለቶችን በማረም በ2017 ዓ.ም የዞኑ የህብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ የዞኑ ፕላንና ልማት መምሪያ አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ዳርጌ ተክሉ በመድረኩ ተገኝተው እንዳሉት በዞኑ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸው መረጃዎችን በመሰብሰና በማደራጀት ረገድ መምሪያው እየሰራቸው ያሉ ስራዎች አበረታች ናቸው።

በዞኑ እየተሰሩ ያሉ ካፒታል ፕሮጀክቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ይበልጥ መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በዞኑ በክልል ደረጃ እየተከናወኑ ያሉ ካፒታል ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር እንዲገቡ ክትትል እንደሚደረግ አንስተዋል።

የጉራጌ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ከበደ ሀይሌ በመክፈቻ ንግግራቸው መምሪያው በ2016 በጀት አመት ከቀረቡለት 290 ፕሮጀክቶች በብር 1ነጥብ 4 ቢሊዮን ውስጥ 97 ፕሮጀክቶች በብር 2885 ሚሊዮን 224 ሽህ 547 ብር በጀት እንዲደገፉ በማድረግ በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቁ ከባለድርሻ አካላት በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በዞኑ የመረጃ ጥራትና ወቅታዊነት ላይ እየተሰራ ያለው ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች መኖሩን ያነሱት ኃላፊው አሁንም በዘርፉ ያለውን ውስንነት ለመቅረፍ ሁሉም በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

መምሪያው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ ካፒታል ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቁ ከባለድርሻ አካላት በቅንጅት እየተሰራ ያለው ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በዘርፉ ውጤታማ ስራ መስራት እንዲቻል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እስከታችኛው መዋቅር በመውረድ ለመስጠት እንደታቀደም አቶ ከበደ አንስተዋል።

በ2016 በጀት አመት የነበሩ ጥንካሬዎች ይበልጥ በማጠናከርና ጉድለቶቹን በማረም በ2017 ዓ.ም የታቀዱ እቅዶችን በማሳካት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት በበጀት አመቱ የነበሩ ጠንካራ ተግባራት በማጠናከርና ጉድለቶችን በማረም በ2017 በጀት አመት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በዞኑ በክልል መንግስት እየተሰሩ ያሉ ካፒታል ፕሮጀክቶች በወቅቱ እንዲጠናቀቁ ክትትል ሊደረግ ይገባል።

ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ለማድረግ የመረጃ ጥራትና ወቅታዊነት ወሳኝ ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ በዚህም በዘርፉ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰሩ አንስተዋል።

በዘርፉ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የሰው ሀይል እጥረት ላይ መምሪያው መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

በመጨረሻም መምሪያው ከወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ጋር የ2017 ዓ.ም እቅድ የግብ ስምምነት ከመፈራረም ባለፈ በ2016 በጀት አመት ከ1 እስከ 3 በመውጣት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መዋቅሮችና ፈጻሚዎች
የዋንጫና የሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *