የዜጎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች አቅም መጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ።

የደቡብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ከክልሉ አመራር አካዳሚ ጋር በመተባበር ሁለተኛውን ዙር የአመራሮች ስልጠና “አዲስ ፖለቲካዊ እይታ ለአዲስ አገራዊ እመርታ!'” በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ መሰጠት ተጀምሯል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና ርዕዮተ አለም ግንባታ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል የዜጎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የአመራሩ የመፈጸምና የማስፈፀም አቅም ለማጎልበት ፓርቲው እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ስለሚሰሩት ስራ እና ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን በመረዳት ህዝቡ የሚጠይቃቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ምላሽ መስጠት እንዲችሉ የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ፓርቲው እየሰጠ ይገኛል።

አክለውም አቶ ስንታየሁ ስልጠናው ከንድፈ ሀሳብ በተጨማሪ በተግባር የተሰሩ ስራዎች በመጎብኘት ልምድ እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል።

በአመራሩ መካከል የነበሩ አመለካከት እና ተግባር አፈጻጸም ልዩነቶች በማጥበብ የአንድነት፣ የወንድማማችነትና የአብሮነት እሴቶች ለማጎልበት ያስችላቸዋል ያሉት አስተባባሪው የአመራሩ የስነ ምግባርና የማስፈፀም አቅም በማጎልበት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ስልጠናው እንደሚያግዛቸው ጠቁመዋል።

የክልሉ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ አስረስ እንደገለጹት አመራሩ በተግባር ሊፈጽሟቸው ያቀዷቸው ተግባራት በእውቀትና በብቃት መፈጸም እንዲችሉ አካዳሚው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

በመሆኑም እየተሠጡ ያሉ ስልጠናዎች በባለፈው የፖለቲካ ርዕዮት በአመራሮች ላይ የሰረጹ የተሳሳቱ ትርክቶች በአዲስ ፓለቲካዊ እይታ እና አስተሳሰብ ለመቀየር ያስችላቸዋል ብለዋል።

በመጀመሪያው ዙር በአራት ክላስተሮች ከአንድ ሺህ 200 በላይ አመራሮች የሰለጠኑ መሆኑና አሁንም በሁለተኛው ዙር ከ9 ሺህ በላይ የሚሆኑ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እየሰለጠኑ እንደሚገኙ አቶ ንጉሴ ገልጸዋል።

የአመራሩ አቅም መጎልበት ሀገሪቱ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ያስችላል ያሉት አቶ ንጉሴ የ2014 በጀት አመት አፈፃፀም በመገምገም የ2015 በጀት አመት እቅድ ከልሶ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል። ዛሬ የተጀመረው ስልጠና ለቀጣይ 5 ቀናቶች እንደሚቀጥል በመጠቆም።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በበኩላቸው ስልጠናው የመንግስትና የብልጽግና ፓርቲ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ሲስተዋሉ የነበሩ ሰህተቶችንና የተዛቡ ትርክቶችን በመደመር እሳቤ ለማረም እንዲሁም አዲስ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት ያስችላል ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *