የዘንድሮው የበጋ የመስኖ ስንዴ ተግባር ከምግብ ፍጆታ በተጨማሪ ወጣቶችና ሴቶች የኢኮኖሚ አቅማቸው እንዲያሳድጉበት በትኩረት እንደሚሰራበት የጉራጌ ዞን ግብርና መምርያ አስታወቀ።

የ2014 አመተ ምህረት በበጋ መስኖ ስንዴ 255 ሄክታር መሬት ለማልማት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የቸሀ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።

በቸሀ ወረዳ የበጋ የመስኖ ስንዴ ማስጀመሪያ ፕሮግራም የክልል፣ የዞን ፣የወረዳ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም አርሶ አደሮች በተገኙበት በወድሮ ቀበሌ በዛሬው እለት ተጀምራል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በዚህ ወቅት እንዳሉት የዘንድሮው የበጋ የመስኖ ስንዴ ተግባር ስራ ከምግብ ፍጆታ በተጨማሪ ወጣቶችና ሴቶች የኢኮኖሚ አቅማቸው የሚያሳድጉበት ይሆናል ሲሉ አሳውቀዋል።

በሀገር ውስጥ የተከሰተው ጦርነት ሊያመጣ የሚችለው የኢኮኖሚ ቀውስ ለመቀነስና የውጭ ስንዴን ለማስቀረት ዞኑ ልዩ ትኩረት በመስጠት ከ2ሺ ሄክታር መሬት በላይ በመስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዷል በዚህም ከ94 ሺ ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል ነው ያሉት።

ሌሎችም የመስኖ ስራዎች ተጠናክረው እየሄዱ ነው ያሉት አቶ አበራ ለአብነትም በአትክልት የመስኖ ስራዎች 50 ሺ ሄክታር ለማልማት ታቅዶ በጥሩ ሁኔታ እየተሰራ እንዳለ አመላክቷል።

ዘመናዊ የመስኖ አውታሮች ፤ትላልቅ የውሃ ፓምፖች እና በባህላዊ ወይም በወንዝ ጠለፋ ዘዴዎችን በመጠቀም የመስኖ ስራው በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝም አቶ አበራ ገልጸዋል።

በዞኑ በ16 ወረዳዎች በ108 ቀበሌዎች ከ6ሺ 400 በላይ አርሶ አደሮች በበጋ መስኖ ስንዴ ያለማሉ ያሉ ሲሆን ስራው በእውቀትና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ለባለሙያ የክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል ብለዋል።

አቶ አበራ አክለውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንባር ሆነው ጦርነቱን እየተፉለሙ ሲሆን ግንባር ያልሄደው አመራር ባለሙያ ፣አርሶ አደር እና መላው ህብረተሰብ ባለበት የስራ መስክ ግንባር ላይ ሊሆን እንደሚገባና ለኢኮኖሚው እድገት የድርሻው መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል ።

የቸሀ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት የዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ተግባር የአመራሩ እና የባለሙያው ወቅታዊ ተግባርና የህልውና ጉዳይ ተደርጎ እንዲሰራበት ተደርጓል።

የውጭ ሀገራት ህዋሀትን እንደ ፈረስ በመጋለብ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ችግር እንዲከሰት የሚያደርጉት እንቅሰቃሴ ለመቀነስና የስንዴ ልመና ለማስቀረት የግብርና ስራው በማጠናከር የበጋ መስኖ ስንዴ በወረዳው የውሃ አማራጭ ባላቸው ቀበሌዎች ተጠናክረው እንዲሰሩ ይደረጋል ብለዋል አቶ ሙራድ ከድር።

በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ 255 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዷል ያሉት አቶ ሙራድ የወረዳው ስራ አጥ ወጣቶች በዚህ ዘርፍ ይሰማራሉ ያሉ ሲሆን ለአብነትም በመገናሴ ቀበሌ 5 የኢንጅነሪንግ ተማሪዎች በስንዴ መስኖ ስራ መደራጀታቸው አሳውቀዋል።

ስራው ውጤታማ ለማድረግ በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ በማድረግ፣ምርጥ ዘር በመስጠት ፣ጀኔሬተሮች በማስጠገን፣ ግብአት በማቅረብ ስራ እየተሰራበት እንደሆነ የገለጹት አቶ ሙራድ ቴክኖሎጂው አዲስ እንደሚሆኑ መጠን የበሽታ ክትትል እንደሚደረግም ተናግሯል ።

የቸሀ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ይልማ እንዳሉት ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት እስካሁን 150 ሄክታር መሬት ዝግጁ ሆኗል ብለው በዛሬው እለት በወድሮ ቀበሌ ደግሞ በ13 ሄክታር መሬት ማስጀመር መቻሉ ጠቁመዋል።

አክለውም በአርሶ አደሩ የክህሎት ክፍተት እንዳይኖር ባለሚያው ወደ ታች በመወረድ ሙያዊ እገዛ እንዲያደርግ በማሰማራት ፣ምርጥ ዘር በማቅረብ፣መሬቱን በማለስለስ፣ግብአት በአግባቡ እንዲጠቀም የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

አርሶ አደር መካ ባዴ ፣ሙራድ መሀመድ እና ወጣት ኤሊያስ የበጋ መስኖ ስንዴ የሚሰሩ አርሶ አደሮች ሲሆኑ የስንዴ ምርት ከዚህ በፊት ለምግብነት ይጠቀሙት እንደነበር አስታውሰው ከጥቂት አመት ጀምሮ ግን ምርቱ እየቀነሰ መምጣቱ ታዝበናል ብለዋል።

በመሆኑም የስንዴ ምርት ከሚሰጠው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በቀጣይ ጊዜ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ማለታቸውን ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

-አካባቢህን ጠብቅ!

  • ወደ ግንባር ዝመት!
  • መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *