የወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዞኑ በአዲስ የተዋቀሩ የፌዴሬሽንና የማህበር አደረጃጀቶች በትኩረት መስራት እንዳለባቸዉም ተገለጸ።

19/2016 ዓ.ም

የጉራጌ ዞን የወጣቶች ፌዴሬሽንና ማህበር ለማጠናከር እና መልሶ ለማደራጀት ዞናዊ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል።

ወጣቶች የአገራችንና የክልላችንን ፈጣንና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ፣ የተሟላ ሠላም ለማስፈንና ቀጣይነት ያለው የዴሞክራሲ ሥርዓት እውን ለማድረግ የወጣቱ ትውልድ ሚና ወሣኝ ነው፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶች ፌዴሬሽንና የወጣቶች ሊግ ስራ አሰፈጻሚ ወጣት አብዱ ድንቁ በጉባኤዉ ተገኝተዉ እንደሉት ወጣቶች ሁለንተናዊ ፣ ተሣትፎውንና ተጠቃሚነቱን የማረጋገጥ፣ በልዩነት ውስጥ አንድነትን የማጎልበት፣ አብሮነታችን ማጠናከር፣ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን በቁርጠኝነት የመታገልና የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለባቸዉም ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ፌዴሬሽን በመገንባት ላይ ባለው ዴሞክራሲያዊ ስርዓትና በሚካሄደው ፈጣንና ዘላቂ
የልማት ሂደት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ሚና ያላቸው እንደመሆናቸው መጠን “መላውን የክልላችን ወጣት የማደራጀት፣

የክልላችን መንግስትና ፓርቲ ለክልላችን ወጣቶች የሰጡት የተለየ ትኩረት መጠቀምና ወደ ውጤት የመቀየር ጉዳይ የአመራሩና የባለ ድርሻ አካላት ሚና የጎላ እንደሆነም አብራርተዋል።

ወጣቶች በቀጣይ ትልልቅ ሀገራዊ አጀንዳዎችና ተልዕኮዎች ተቀብሎ መፈፀም የሚችል ጠንካራና በህዝብ ውስጥ ሆኖ የሚሰራ ከቀበሌ እስከ ዞን ድረስ የተመረጡ የወጣት አደረጃጀቶች፣ አመራሮችና ስራ አስፈፃሚዎች ለስኬታማነቱ ከመቼዉም ጊዜ በላይ በቀንጅት መስራት እንዳለባቸዉም አብራርተዋል።

በጉባኤዉ የተገኙት የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን እንዳሉት በዛሬ እለት በዞን ደረጃ የወጣቶች አደረጃጀት ፎረምና የወጣቶች አደረጃጀት ፌዴሬሽንና ማህበር መልሶ የማቋቋምና በስራ ምከንያት ወደ ሌላ አካባቢ ሰዎች በቦታቸዉ የመተካት ስራ ተሰርቷል።

ይህንንም አደረጃጀት በተመለከተ በወረዳ እና ከተማ ደረጃ በአዲስ መልክ የማደራጀቱ ስራ የተሰራ ሲሆን ዛሬ በዞን ደረጃ ጉባኤ መካሄዱም ተናግረዉ ወጣቱን በማደራጀት መሪ ኖሮት ወጣቶች በሁሉም ዘርፎች ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድግረግ እንደሚገባመ አመላክተዋል።

የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማጎልበት ከመቼዉም ጊዜ በላይ አጽኖት ተሰጥቶት እየተሰራና ወጣቶች በአካባቢ ልማትና ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ማገዝ አለበቸዉ ብለዉ ወጣቶች የወጣትነት ጊዜያቸዉ በተገቢዉ በመጠቀም እራሳቸዉንና ማህበረሰቡን መጥቀም እንዳለባቸዉም ተናግረዋል።

በዚህ አደረጃጀት በዞኑ የሚገኙ ወጣቶች በሁሉም ዘርፎች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሁም አልሚም እንዲሆኑ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ትኩረት እንደሚሰራም አብራርተዋል።

የወጣት አደረጃጀቶች የወጣቱ ስብዕና በመገንባትና በተለያዩ ዘርፎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባም አስረድተዋል።

የተመረጡ የፌዴሬሽንና የማህበር አደረጃጀቶች ወጣቶች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አበክረዉ መስራት እንዳለባቸዉም ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣት ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ደገፈ ደበሮ ወጣቶች በሀገር ልማትና ዕድገት ላይ ግንባር ቀደም መሆን አለባቸዉ ብለዉ ወጣቶችን የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርጉ አማራጮችን ማመቻቸት እንዳለባቸዉም አንሰተዉ የወጣቱ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ፣ የወጣቱ ስነ ምግባር በማሻሻል የበኩላቸዉን መወጣት አለባቸዉ ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙ አንዳንድ ባለድርሻ አካላት በሰጡት አሰተያየት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በአደረጃጀቶች ዘርፍ የሚፈለገዉን ለዉጥና ዉጤት ማምጣት እንደሚገባም አመላክተዋል።

እንደ ሀገር ለወጣቱ መንግስት የሰጠዉ ትኩረት የሚበረታታ እንደሆነም ተናግረዉ ወጣቱ በፌዴሬሽንና በማህበር አደረጃጀት በማሳተፍ ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ ማረጋገጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የሀገራችንን ሰላም ለማሰከበር የወጣቱ አመለካከት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አስረድተዉ በዚህም የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ በቅንጅት መስራትም እንደሚገባም አሰታዉቀዋል።

በጉባኤዉ ማጠቃለያ ለወጣቶች ማህበር ስራ አስፈጻሚ
ወጣት ሙባሪክ ጀማል ፣ሙኒራ ሞሳ፣ ሀብታሙ ወልዴ ፣ሸምሱ ሻፊ ፣ትግስት ፍሬ፣ ጌታቸዉ ታበዙ፣ ቸሩ ፍቃዱ፣አሸናፊ በስር፣ አብድልከሪም ተመርጠዋል።

እንዲሁም ለወጣቶች ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚዎች
ወጣት ሰፊ ቅባቱ፣ ሙባሪክ ጀማል ፣ሙኒራ ሞሳ ፣መኪ ሀሰን ፣አብራሀም ሞሼ ፣በላይነህ ሰልማን፣በሀዉ ህያር፣ ረመዳን አብድላ ፣ጀማል ሀይሩ ተመርጠዋል።

በመጨረሻም ቀደም ሲል የዞኑ ወጣቶች ፌዴሬሽን የነበሩት ወጣት አብዱ ድንቁ ለወጣት ሰፊዩ ቅባቱ የስራ ርክክብ አድርገዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *