የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኮሌጅ በ2017 ዓመተ ምህረት በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች የሚያሰለጥናቸዉ ተማሪዎች እየተቀበለ ይገኛል።
ኮሌጁ የአካባቢ ጸጋን መሰረት ባደረገ መልኩ ገበያ ተኮር የሆኑ ስልጠናዎች በመስጠት ወጣቶች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ከስራ ጋር የማስተሳሰር ስራ በስፋት እየሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።
በተያዘዉ በጀት አመት ከ2 ሺህ 5 በላይ ሰልጣኞች በመቀበል ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል።
የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኮሌጅ ዲን አቶ ሀይሩ አህመዲን እንዳሉት በ2017 ዓመተ ምህረት በተለያዩ የስልጠና ዘርፎ ሰልጣኞች ተቀብሎ ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ በዛሬዉ እለት ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል።
የአካባቢ ጸጋን መሰረት ባደረገ መልኩ ገበያ ተኮር የሆኑ ስልጠናዎች በመስጠት ወጣቶች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ከስራ ጋር የማስተሳሰር ስራ ይሰራል ብለዋል።
በተያዘዉ አመት ከ2 ሺህ 5 በላይ ሰልጣኞች በመቀበል ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል ብለዉ ከ2016 በተለየ ሁኔታ አጠቃላይ የተቋሙ ስራዎች ዲጂታላይዝድ ለማድረግና የኔትወርክ መሰረተ ልማት በሀይብርኦብቲስ የመቀየር ፣ አዳዲስ የስለጠና ዘርፎች ጭምር በማስገባትና በዞንግ ዲፈረንሴሽን የአካባቢ ጸጋ መሰረት ያደረጉ ስልጠና ሙሉ ትግበራ ለመጀመር እየተሰራ መሆኑም አመላክተዋል።
ሰልጣኞች በተቋሙ ሰልጥነዉ ሲወጡ ከስራ ጋር የማስተሳሰር ስራ የሚሰራ እንደሆነም አስታዉሰዉ ከዛሬ ጥቅምት 19/2017 ዓመተ ምህረት እስከ 22/2017 አመተ ምህረት ሰልጣኞች እንዲመዘገቡ በሞንታርቦና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች የቅስቀሳ ስራ የተሰራ መሆኑም ተናግረዋል።
አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎች በሚፈልጉት ዲፓርትመንቶች መርጠዉ እየተመዘገቡና ለተማሪዎች አጠቃላይ ኮሌጅ እየሰራዉ ያለዉ ስራ ግንዛቤ የመፍጠር ስራም እየተሰራ መሆኑም አብራርተዋል።
የቴክኒክና ሙያ ተቋማቶች በአለም አቀፍና በሀገራችን ተመራጭ እየተደረገ እንደሆነም ጠቁመዉ በቴክኒክና ሙያ የተመረቀ የሰዉ ሀይል በሀገር ዉስጥና በዉጭ ሀገር የስራ ዕድል የማግኘት ሁኔታ በጣም ከፍተኛ መሆኑም አብራርተዋል።
ክህሎትና የቢዝነስ ሀሳብ ሳይጨብጡ ወደ ስራ መሰማራት የማይቻልበት ወቅት መሆኑም ያስረዱት ዲኑ በኮሌጁ በዚህ አመት ከ2 ሺህ 5 መቶ በላይ ሰልጣኞች የሚቀበሉና ነባር ሰልጣኞችም በተገቢዉ ስልጠናቸዉ እየተከታተሉ መሆኑም አመላክተዋል።
ከቦሌለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሻት ጋርመንት ፋብሪካ ጋር በዚህ አመት ከተቋሙ የተመረቁ ከ80 በላይ ሰልጣኞች በቀጥታ ስራ ዕድል የተፈጠረላቸዉ መህኑም ያስታወሱት ሀላፊዉ ከካንስ ኢንጅነሪንግ ጋር በመሆን በአቶሞቲቭና በብረታ ብረት የሰለጠኑ ልጆች ወደ ስራ የማስገባት ስራም እንደሚሰራና እንዲሁም የቆጮ ማሽን የሚያመርቱ ልጆች በማደራጀት ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
ኮሌጂ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሙያ መስመሮች በመደበኛ፣ በዊኬንድና በማታ ፕሮግራሞች ሰልጣኞችን እየተቀበለ ይገኛል።
👉በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በሆቴልና ቱሪዝም ቴክኖሎጂ ከደረጃ1-4
👉በኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በሜታል ማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በጋርመንት ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በቴክስታይል ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-4
👉በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በኢኮኖሚክ ኢንፍራስትራክቸር ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በአርባን ግሪነሪ ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-4
👉በሌዘርና ቆዳ ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-2
👉በሶላር ፒቪ ሲሆን አመልካቾች ወደ ተቋሙ በአካል እየመጡ እየተመዘገቡ ይገኛል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽንና መምሪያ ነዉ።