የወልቂጤ ዲስትሪክት ኦሞ ማይክሮ ፅህፈት ቤት በደቡብ ክልል ከሚገኙ 19 የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ዲስትሪክቶች በ2013 ዓ.ም አጠቃላይ የተግባር አፈፃፀም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ዘንድሮም ለ5ኛ ጊዜ ደረጃውን በማስጠበቅ ተሸላሚ መሆኑን አስታወቀ።

የደቡብ ክልል የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ሰሞኑን ባካሄደው አጠቃላይ አመታዊ ጉባኤ ላይ የወልቂጤ ዲስትሪክት ፅህፈት ቤት ከግማሽ ሚለዮን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስና የጥሬ ገንዘብ የማበረታቻ ሽልማት ማግኘቱ ዲስትሪክቱ ገልጿልም።
የወልቂጤ ዲስትሪክት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በለጠ ሀይሌ ከደቡብ ክልል ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ የተደረገላቸው እውቅናና ሽልማት ከፅ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር ርክብክብ ሲያደርጉ እንደገለፁት በ2013ዓ.ም በደቡብ ክልል ኦሞማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ስር ከሚገኙ 19 ዲስትሪክቶች መካከል የወልቂጤ ዲስትሪክት በተቋሙ በተጣሉ ግቦች የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ገልፀዋ።
በባለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት በአፈፃፀም ግንባር ቀደም እንደነበረ ገለፀው ዓምና በነበረው አለም አቀፋዊና ሀገራ ክስተቶች ደረጃውን አስጠብቆ ለማስቀጠል ፈታኝ ቢሆንም በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ውጤታማ መሆን መቻላቸውን ተናግረዋል።
ዘንድሮ ለየት ባለ መልኩ ከዲስትሪክቱ ባሻገር በክልሉ ከሚገኙ 232 ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች መካከል በወልቂጤ ዲስትሪከ ስር የሚገኙ የሶዶ፣የአበሽጌና እንደጋኝ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች እንደቅደም ተተላቸው ከአደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ በመውጣት ተሸላሚ ሁነዋል ብለዋል።
በዚህም ከዋንጫና ሜዳሊያ በተጨማሪ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ዴስክቶፖ ኮሞፒውተሮች ከነፕሪንተራቸው ፣እሰካነሮች፣ ሌሎች ቁሳቁሶችና የጥሬ ገንዘብ ማበረታቻ ሽልማቶች ማግኘታቸውን አብራርተዋል።
በበጀት ዓመቱ ከ537 ሚለዮን ብር በላይ ቁጠባ ለማሰባሰብ ታቅዶ ከ1 ቢሊዮን 238 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የገለፁት ኃላፊው ይህ ከአምና ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ27 በመቶ ጭማሪ እንዳለው አስታውቀዋል።
ተቋሙ ከ204 ሚሊዮን ብር ብድር ለማሰራጨት አቅዶ ከ431ሚሊዮን ብር በላይ ማሰራጨት መቻሉን የገለፁት አቶ በለጠ ኃይሌ ብድር በማስመለስና በሌሎች ተግባራትም ከእቅድ በላይ ማሳካት መቻላቸው አብራተዋል።
አክለውም በተገኘው ውጤት ደስተኛ መሆናቸውና ለቀጣይ ስራ ከፍተኛ መነሳሳት እንደሚፈጥርላቸው የተናገሩት ኃላፊው ህብረተሠቡን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ እንሠራለን ብለዋል።
የተገኘው ውጤቱ የመላው ሰራተኞች የትጋት ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በቀጣይ ብሄራዊ ባንክ ባስቀመጠው መሰፈርት መሠረት ወደ ባንክ ደረጃ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ መጠቆም።
የወልቂጤ ዲስትሪክት ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የኦፐሬሽን ማናጀር አቶ አበበ ሀብቴ በበኩላቸው በዲስትሪክቱ ስር የሚገኙ የህበረተሰብ ክፍሎችን በብድርና ቁጠባና በሌሎች አገልግሎቶች በተሻለ መልኩ በማገልገል የተገኘ ውጤት በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደተሠማቸው ገልዐዋል።
በዲስትሪክቱ ከተጣሉ ግቦችን ከአቅድ በላይ ማሳካት የተቻለው በየደረጃው ካሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በተሠራው ቅንጅታዊ ስራ የተመዘገበ ውጤት ነው ብለዋል።
ተሸላሚ ከሆኑ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች መካከል የአበሽጌ ወረዳ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ኦፕሬሽን ማናጀር አቶ ደግፌ ጉንፋ ለደንበኞች ቀለጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም በብድር ስርጭትና እዳ አመላለስ እሰከ ቀበሌ ደረስ ከፍተኛ ንቅናቄ ተፈጥሮ በመሠራቱ በጽህፈት ቤቱ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል ።
በተገኘው ውጤት በቀጣይ የነበሩ ጉድለቶችን በመቅረፍ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ ህብረተሠቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሠሩ ተናግረዋል ።
አቶ አብረሃም መቻል የወልቂጤ ዲስትሪክቱ የሠው ኃይል አሰተባባሪ ሲሆኑ በበጀት ዓመቱ የታቀዱ እቅዶችን ለማሳካት በጥናት በተመሠረተ መልኩ የሠዉ ኃይሉን በበቂ ሁኔታ በማዘጋጀት በየወቅቱ የሚገጥሙ የአፈፃፀም ጉድለቶችን ገምግሞ በመከለስ እና ቀልጣፋ የመረጃ ቅብብሎሽ ስርዓት መዘርጋቱን ተናገረዋል ።
አቶ አብረሃም አክለውም ለተመዘገበው ወጤት በዋናነት ተቋማዊ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሠራቱ ጉልህ ሚና እንደነበረው ጠቁመዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *