የወልቂጤ ዩንቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለማህበረሰቡን እየሰጠ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለፀ።

በተቋሙ ውስጥ እየተሰጠ ባለው የአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ዩንቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውይይት ተካሂዷል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አብድራሂም በድሩ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ሆስፒታሉ ስራ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት አቅዶ እየሰራ ነው ብለዋል።

በውይይቱም ሆስፒታሉ በሁለት አመት የሰራቸው ስራዎችንና ያስመዘገባቸው ስኬቶችን ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠርና ቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆነንም አስረድተዋል።

ማህበረሰቡ ያነሳዋቸው ጥያቄዎችን በመውሰድ በቀጣይ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንዳለበት ያሳሰቡት እንዲህ አይነት ውይይቶች በሆስፒታሉ ውስጥ እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት ለማሻሻል የሚረዳ በመሆኑ በቀጣይ በየ3 ወር እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።

ሆስፒታሉ ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የበጀትና የግብአት እጥረት ተግዳሮት እንደሆነባቸውም አንስተዋል።

በቀጣይ ሆስፒታሉ የስፔሻሊቲና የሰብ ስፔሻሊቲ አገልግሎት ለመስጠት አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመው የሆስፒታሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ሁሉንም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ዶ/ር አብድራሂም አሳስበዋል።

አያያዘውም በሆስፒታሉ የሚሰጡ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የቁጥጥር ስራ መዘርጋቱንና በቀጣይም በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል።

ተቋሙ እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ አስተዋጽኦ ላደረጉ የዩንቨርስቲው የማኔጅመንት አካላት፣ ለዞኑ ጤና መምሪያ፣ ለዞኑ መንግስት፣ ለአከባቢው ማህበረሰብና ሌሎችም እገዛ ላደረጉ አካላት አመስግነዋል።

የውስጥ ደዌ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የውስጥ ደዌ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ሪያድ ኢብራሂም በበኩላቸው ሆስፒታሉ በተመሰረተ በሁለት አመት ውስጥ እየሰጠ ያለው አገልግሎት የሚበረታታና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

አክለውም በሆስፒታሉ የሲቲ ስካና የMRI አገልግሎት መስጫ መሳሪያ ባለመኖሩ መቸገራቸውን ገልፀው ችግሩን ለመቅረፍ በቅንጅት መሰራት እንዳለበትም ጠቁመዋል።

ወ/ሮ ሳአዳ ሁሴን ከእምድብር ከተማ፣ አቶ ጀማል ከወልቂጤ ከተማ፣ ግርማ አበበ ከአበሽጌ ወረዳ በውይይቱ የተሳተፉ ሲሆን በጋራ በሰጡት አስተያየት በውይይቱ ግንዛቤ ማግኘታቸውና ውይይቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጠቁመዋል።

በሆስፒታሉ የውስጥ ገቢ እየተሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ያነሱት ተሳታፊዎቹ በቀጣይም ማህበሰቡ ሆስፒታሉ መንከባከብና በሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ ከሆስፒታሉ ጎን መቆም እንዳለባቸውና መንግስትም ለሌሎች ሆስፒታሎች የሚያደርገውን እገዛ ለሆስፒታሉ ማድረግ አለበት ብለዋል።

አክለውም በሆስፒታሉ ውስጥ የሚስተዋለውን የግብአት እጥረት ለመቅረፍ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበትም አንስተዋል።

በውይይቱም የዞን ጤና የመምሪያ ባለሙያዎች፣ የዩንቨርስቲው የማኔጅመንት አካላት፣ ከአጎራባች ወረዳና ቀበሌ የተወጣጡ የህብረተስብ ክፍሎች፣ የሆስፒታሉ ሰራተኞችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *