የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ “ጀፎረ ኢትዮጵያ ጆርናል አፕላይድ ሳይንስ” የተሰኘ ጆርናል ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በይፋ አስመርቋል።

ዛሬ የተመረቀው ጆርናል አካባቢውና ማህበረሰቡ ከማስተዋወቁም ባለፈ ጆፎረን በአለም ቅርስነት እንዲመዘገብ በሚደረገው ጥረት ሚናው የላቀ እንደሆነ ተገልጿል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል እንዳሉት ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን የማህበረሰቡን እሴት፣ ባህልንና ታሪክ የመጠበቅና የማስተዋወቅ እንዲሁም ሀገር በቀል እውቀቶችን በማሰባሰብ፣ በመጠበቅና በማበልጸግ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ጆርናል ሲያቋቁም ጀፎረ የሚል ስያሜ መስጠቱን ጠቁመው ጀፎረ ህብረተሰቡ በሀዘንና በደስታ ተገናኝቶ የሚመክርበት፣ ሀሳብ የሚለዋወጥበት፣ ስለ ፍትህ የሚደመጥበት፣ ያጠፋ የሚቀጣበትና ብዙ ባህሪያት ያለው በመሆኑ የጆርናሉ ስያሜ ጀፎረ በሚል መሰየሙን ተናግረዋል።

ጀፎረ ኢትዮጵያን ጆርናል አፕላይድ ሳይንስ መጀመሩ ጀፎረን በማስተዋወቅ በአለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ዩንቨርስቲው በጀፎረ ላይ ጥናትና ምርምር ከማድረግ ባለፈ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በአለም ቅርስነት ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሐንስ ገብሩ በበኩላቸው ጀፎረ ኢትዮጵያ ጆርናል አፕላይድ ሳይንስ ለመጀመር የኤዲቶሪያል ፖሊሲ ማጸደቅ፣ የጆርናሉ ዌብሳይት ማዘጋጀት፣ በሀገሪቱ ያሉ ታዋቂ ፕሮፌሰሮች፣ ኤዲተርና ቺፍ ኤዲተር የማካተት ስራ ሲሰራ ቆይቷል።

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰሩ የምርምር ስራዎችን ሼልፍ ላይ ከማስቀመጥ ባለፈ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑና ለህግ አውጪዎች እንዲደርሱ በጆርናል መልክ መታተማቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተጠቁሟል።

ጆርናል ፕሮጀክቶችን ለማሸነፍ ሆነ ሌሎች አካባቢዎች ያሉትን ፕሮጀክቶችን ወደ አካባቢያችን ለመሳብ ሚናው የላቀ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ምርምር ጆርናሎች ኤዲተር ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅና በትምህርት ሚኒስተር ምርምርና ስርጸት አስተባባሪ ዶክተር አቡኖ አረጋ በበኩላቸው በዩንቨርስቲዎችና በምርምር ተቋማት የሚሰሩ ምርምሮች ላይብረሪ ላይ ከማከማቸት ባለፈ የህዝቡን ችግር መፍታት ላይ ውስንነት መኖሩን ጠቅሰው ይህን ለማስቀረት ትምህርት ሚኒስቴር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

የምርምር ጆርናሎች በዩኒቨርሲቲዎችና በምርምር ተቋማት ውስጥ ከ2 መቶ በላይ የሀገር ውስጥ ጆርናሎች መኖራቸውን ጠቅሰው ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት ያስመረቀው ጆርናል ሁሉም ፊልድ ያካተተ በመሆኑ ይህም ዘላቂነት ባለው መልኩ አጠናክሮ በመስራት ጥራት ያለው የምርምር ውጤቶችን ለማህበረሰቡ ለማቅረብ ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የጀፎረ ኢትዮጵያን ጆርናል አፕላይድ ሳይንስ ዋና አዘጋጅ ዶክተር ጌታቸው መኮንን በበኩላቸው ዩኒሸርሲቲው ከአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ሪሰርች ዩኒቨርሲቲ ለማሳደግ ጆርናሉ መፍጠር መቻሉን ጠቁመው ጆርናሉ ኦንላይን መሆኑ ጠቅሰው በርካታ አለም አቀፍ እውቅና ያላቸው 11 አማካሪ ፕሮፌሰሮች ያቀፈ ቦርድ ማቋቋም ተችሏል ነው ያሉት።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያውን ጆርናል ማስጀመሩን አመስግነው ጀፎረ በሚል ያስመረቀው ጆርናል ጀፎረ እንዲተዋወቅ ከማድረጉም ባለፈ ምሁራኖች በዘርፉ ስራዎች እንዲሰሩ ያበረታታል ማለታቸው የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነወ።

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Tiwter https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *