የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ጋር በመተባበር የትራፊክ አደጋ መቀነስ የሚያስችል ስልጠና ለባለድርሻ አካላቶች እየሰጠ እንደሆነ ተገለጸ።


ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳድር የተዉጣጡ መንገድ ልማት ባለሙያተኞች ፣የትራፊክ የቁጥጥር ባለሙያተኞች ፣ፖሊሶች ፣የትመህርትና የጤና ቢሮ ሀላፊዎች መምህራኖች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላቶች በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ስልጠናዉ እየወሰዱ እንደሆነም ተጠቁሟል።

እግረኞች ግራ ጠርዝ በመያዝ ፣ እንዲሁም አስፓልት ሲያቋርጡ ዜብራን እንዲጠቀሙና አሽከርካሪዎች ከተፎደላቸዉ ፍጥነት በላይ እንዳያሽከረክሩ ተገቢዉን ግንዛቤ መስጠት ይገባል።

የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ከድር እንዳሉት የአሽከርካሪዎች ጥንቃቄ አለመኖር በእግረኞች ቸልተኝነት ከፍተኛ አደጋ እየተፈጠረ እንደሆነም አስረድተዋል።

ስልጠናዉ በዋናነት በተሽከርካሪዎችና በእግረኞች መካከል ባለዉ የግንዛቤ እጥረት ምክንያት ያለ አግባብ እየተፈጠረ ያለዉ የሰዉ ህይዉት መጥፋትና የንብረት ዉድመት ለመቀነስ የሚያስችል ስልጠና ነዉ።

የመንገድ ባለድርሻ አካላቶች በማቀናጀት የትራፊክ አደጋ መቀነስ እንደሚገባም ያብራሩት ሀላፊዉ በዞኑ በ2015 ዓመተ ምህረት ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ አደጋ እየተከሰተ እንደሆነም አብራርተዉ በዚህም የበርካታ ሰዎች ህይወት የጠፋና ከፍተኛ የሆነ የንብረት ዉድመት መድረሱም አስረድተዋል።

የግንዛቤ ስልጠና የወሰዱ ባለድርሻ አካላቶች በስልጠና ቆይታቸዉ ያገኙትን እዉቀት ተጠቅመዉ ለማህበረሰቡ ለተማሪዎችና ለአሽከርካሪዎች ግንዛቤ በሰፊዉ መስራት እንዳለባቸዉም አሳስበዋል።

በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች እግረኞች ግራ ጠርዝ በመያዝ ፣ እንዲሁም አስፓልት ሲያቋርጡ ዜብራን እንዲጠቀሙ ተገቢዉን ግንዛቤ መስጠት እንደሚገባም አብራርተዋል።

አሽከርካሪዎች የመንገድ ዳር ምልክቶችን በአግባቡ በመጠቀም ከተፈቀደዉ በላይ ፍጥነት ባለመጠቀም በሰዉ ሀይወትና በንብረት ላይ የሚደርሰዉን አደጋ ሞነስ እንደሚገባም አስረድተዋል።

የትራፊክ አደጋ በዋናነት በተማሪዎችና በአምራቹ ሀይል ላይ እየደረሰ ሲሆን ለዚህም በትምህርት ቤቶች አካባቢ መንገድ ዳር በሚገኙ ገበያዎች ላይ በተገቢዉ ግንዛቤ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም አብራርተዋል።

በመጨረሻም አቶ ሙራድ ስልጠናዉን ያመቻቸላዉ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን አመስግነዉ በቀጣይም በትራፊክ ረደጋ መቀነስ የሚያስችል መሰል ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ከዩኒቨርሲቲዉ ጋር በመሆን የተሻለ ስራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመንገድና ደህንነት ባለሙያና አሰልጣኝ አቶ እስማኢል ሰኢድ እንዳሉት በአለም አቀፍና በኢትዩጵያ በትራፊክ አደጋ በሚሊየን የሚቆጠሩ የሰዉ ልጆች እየቀጠፈ ይገኛል።

የትራፊክ አደጋ ከሞት በተጨማሪ በሰዎች ላይ የአካል ጉዳትና የስነ ልቦና ቀዉስ ያስከትላል ብለዉ በተለያዩ ጊዜያት በሚፈጠሩ የትራፊክ አደጋ አብዛኛዉ አምራቹን ሀይል እየቀጠፈ እንደሆነም አመላክተዋል።

ዩኒቨርሲቲዉም ይህንኑ አደጋ ለመቀነስ መልካም ተሞክሮዎችንና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸዉ ትምህርቶች ለዘርፉ ባለድርሻ አካላቶች ከዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልሜት መምሪያ ጋር በመቀናጀት የግንዛቤ ስልጠና እየሰጡ እንደሆነም አብራርተዋል።

በዚህ ስልጠና ላይ የዞኑ መንገድ ልማት ባለሙያተኞች ፣የትራፊክ የቁጥጥር ባለሙያተኞች ፣ፖሊሶች ፣የትመህርትና የጤና ቢሮ ሀላፊዎች መምህራኖች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላቶች በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ስልጠናዉ እየወሰዱ እንደሆነም አስረድተዋል።

የስልጠናዉ ዋና አላማ መቀነስ የሚቻልበት የቅንጅታዊና አሰራርን ለባለ ድርሻ አካላት በመጠቆም የተሻለ ስራ ለመስራት አላማ ያለመ እንደሆነም አስታዉቀዉ ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ የሚሰራበትም እንደሆነም አብራርተዋል።።

በስልጠናዉ ያነጋገርናቸዉ አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያተኞች በሰጡት አስተያየት በዞኑ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ የሚስተዋል ሲሆን ይህንኑም ለመቀነስ የተመቻቸላቸዉ የግንዛቤ ስልጠና አጋዥ እንደሚሆናቸዉም አመላክተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *