የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጤናና ጤና ነክ ጉዳዮች ላይ በርካታ የህክምና አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ ፡፡

በሆስፒታሉ የቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ሲሆን ከዚህ ቀደም ህብረተሰቡ አገልግሎቱን ለማግኘት ያላስፈላጊ ወጪና እንግልት ይዳረግ እንደነበር የገለጹት የስራ ክፍሉ ኃላፊ ደ/ር መከተ ወንድወሰን ሆስፒታሉ ስራ ከጀመረ ወዲህ በርካታ ዜጎች እፎይታን ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

በሆስፒታሉ በቀዶ ጥገና ህክምና ክፍል ውስጥ አምስት የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስቶች፣ ሁለት የአጥንት ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስቶችና አሁን በቅርቡ የሚጀምር አንድ የህፃናት የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ዶ/ር መኖሩን ዶ/ር መከተ ተናግረዋል።

ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመስጠት የጤና ችግር ለመቅረፍ እንዲቻል ከተገልጋይ የሚሰጡ አስተያየቶችንና ቅሬታዎችን በመቀበል የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም ያልነበሩ ተጨማሪ የህክምና ግበአቶችንና ማሽኖችን በማሟላት ለዜጎች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በቀዶ ጥገና ህክምና የስራ ክፍል የድንገተኛ ቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ለተመላላሽ ታካሚዎች በስራ ቀናት ለ5 ቀን የቀዶ ጥገና አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል።

በተያያዘ ዜና በቀጠሮ መጥተው ለሚታከሙ ታካሚዎች በሳምንት 3 ቀን አገልግሎቱ የሚሰጥ ሲሆን በቀን 3 ክፍል ውስጥ በመስራት በሳምንት 9 ጊዜ የቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት ይሰጣል ሲሉ ኃላፊው አብራርተዋል።

በሆስፒታሉ ከሚሰጡ የቀዶ ህክምና አገልግሎቶች መካከል የእንቅርት እጢዎችን፣ እባጮችን፣ ትርፍ አንጀት፣ የአንጀት መታጠፍ፣ የአንጀት ትቦ መዘጋት፣ በተለያየ የሰውነት ክፍል ላይ የሚወጡ እባጮች፣ የደረት ላይ ደም መርጋት፣ የሀሞት ጠጠር፣ ስብራት፣ ካንሰር፣ በድንገተኛ አደጋ የጭንቅላት መመታትን ጨምሮ ድንገተኛ አደጋዎች የቀዶ ጥገና ህክምና እንደሚሰጥ ከሆስፒታሉ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መረጃው የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፌስቡክ ገጽ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *