የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚሰጠው አገልግሎት በማሻሻል ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታወቀ።

ሆስፒታሉ ወቅታዊ ተዓማኒነት ያለውና ጠቃሚ የጤና መረጃዎች ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡ ለማንቃት ከሚዲያ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ እንደሚሰራ ተገለጸ።

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከመማር ማስተማር ስራው በተጨማሪ የህብረተሰቡን ጤና ለማጎልበት የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ሆስፒታሉ በቀጣይ አምስት አመታት የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ደረጃውን በማሻሻል በህክምናው ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ለማበርከት ግብ ጥሎ እየሰራ መሆኑን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር አብድረሂም በድሩ ገልጸዋል።

ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ሁለት አመታት ማስቆጠሩን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ባይጠናቀቅም ለ101 ሺህ 353 የህብረተሰብ ክፍሎች ከቀላል ህክምና እስከ ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት መስጠት እንደቻለ አስረድተዋል።

በሚቀጥሉት አምስት አመታት የሆስፒታሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ደረጃ ለማሳደግ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ተጨማሪ የትምህር ክፍሎች ከመክፈት ባሻገር የአይን፣ የስነ አእምሮ፣ የኩላሊት፣ የልብ፣ የህብረ ሰረሰር፣ የፊዚዮ ቴራፒና የሌሎች ስፔሻሊስት ህክምና አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን ዶክተር አብድረሂም ገልጸዋል።

ሆስፒታሉ አዲስና በቁሳቁስ የተሟላ ባለመሆኑ ህብረተሰቡ የሚፈልገው የህክምና አገልግሎት መስጠት እንዳልተቻለ የተናገሩት ስራ አስኪያጁ ሆስፒታሉ በቁሳቁስ በማሟላት ህብረተሰቡ የሚፈልገውን አገልግሎት ለመስጠት በቅርበት ሊደግፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዩኒቨርስቲው የማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብዓዊ ኮሌጅ መምህር ሪድዋን ነጃ የሆስፒታሉ ወቅታዊ ተዓማኒነት ያለውና ጠቃሚ የጤና መረጃዎች ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡ ለማንቃት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽና የሚዲያ ተቋማት በባለቤትነት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

መምህር ሪድዋን ” ሆስፒታሉ የኔ ነው! ” በሚል መሪ ቃል ለዞኑ ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ባለሙያዎች በጤና ተግባቦት ስልጠና በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት ህብረተሰቡ የሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ለማሳደግ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችል የሆስፒታሉ ወቅታዊና ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎች እንዲያገኝ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች በባለቤትነት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ይህ ደግሞ በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ከማረም በተጨማሪ ግለሰብ እና ማህብረተቡ ለማነሳሳት፣ የባህሪ ለውጥ ለማምጣት፣ እውቀትና ግንዛቤ ለማሳደግ ያስችላል ብለዋል።

ሆስፒታሉ ደግሞ ለህዝቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ የሚዲያ አማራጮች መጠቀም አለበት ብለዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ሆስፒታሉ ባለፉት ሁለት አመታት ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ ቢሆኑም ስራዎቹ በሚዲያ ተደራሽ ባለመሆናቸው ህብረተሰቡ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ እንዲሆን አስችሎታል ብለዋል።

በመሆኑም በቀጣይ “ሆስፒታሉ የኔ ነው።” የሚለውን መሪ ቃል ተግባራዊ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ መረጃዎች ወደ ማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰሩም ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= አካባቢህን ጠብቅ!
= ወደ ግንባር ዝመት!
= መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *