የህልዉና ጦርነቱ አስኪጠናቀቅ ድረስ የሚያደርጉት ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረዉ እንደሚያስቀጥሉ የወልቂጤ ከተማ ሴት ተናገረዋል።
በስንቅ ዝግጅቱ ላይ የተገኙት የወልቂጤ ከተማ ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሰላም ፍቃዱ እንዳሉት የህልዉናዉ ጦርነት እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸዉም አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ነው።
በበሶዉ ዝግጅት ስራ 580 ሴት የመንግስት ሰራተኞች እና 2 ሺህ 980 በልማት ቡድን የተደራጁ ሴቶች መሳተፋቸውን የገለጹት ኃላፊዋ በግንባር እየተዋደቀ ላለዉ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ለ5ኛ ጊዜ በገንዘብ ፣ስንቅ በማዘጋጀትና በማቀበል የበኩላቸዉን እየተወጡ እንደሆነም አስታውቀዋል።
በዚህም ዙር ከ 5 ነጥብ 5 ሚዮን ብር በላይ ከተለያዩ የሴት አደረጃጀቶች ከማሰባሰብ ባሻገር በጉልበታቸውና ጊዜአቸውን መስዋዕት በማድረግ በተባበረ ክንድ በሶ እያዘጋጁ እንደሆነ ተናግረዋል ።
ለ5ኛ ዙር በግንባር ህይወቱን መሰዋትነት ለመክፈል እየታገለ ላለዉ መከላከያ ሰራዊት በሚደረገዉ የበሶ ዝግጅት ላይ እየተሳተፉ ካሉ ሴቶች መካከል ወይዘሮ ቀለሟ ተረፈ እና ወይዘሮ ስንዱ ታደሰ ይገኙበታል።
ሁለቱም በሰጡት አስተያየት ጁንታዉ ሀገራችን ለመበታተን እየሰራዉ ያለዉን ተንኮልና ሴራ ለመታደግ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ህይወቱን መሰእዋትነት እየከፈለ እንደሆነም ተናገረዋል።
በዚህም መላዉ የወልቂጤ ከተማ ህዝብና ባለሀብት ፣ የመንግስት ሰራተኞች የእርድ ሰንጋ በማቅረብ ፣ ደረቅ ምግብ በማዘጋጀትና በማቀበል ረገድ አርአያነት ያለዉ ተግባር እየተከናወነ እንደሆነም አስታዉቀዋል።
የህልዉና ጦርነቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሰራዊቱን በመደገፍ ረገድ ከመቼዉም ጊዜ በላይ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም አብራርተዋል።
ከዚህም በተጨማሪም ከሰለጠነው የከተማው ህዝባዊ ሰራዊት ጋር በመሆን የቸካባቢያቸውን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ ተናግረዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።
_, አካባቢህን ጠብቅ፣
- ወደ ግንባር ዝመት፣
- መከላከያን ደግፍ።
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡ Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx