የክቡር ሌ/ጄኔራል ወ/ስላሴ በረካ የመታሰቢያ ሀውልት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በጉብርየ ክፍለ ከተማ አደባባይ ተገንብቶ “የምርቃት ስነስርዓት የሀገርና የህዝብ ባለውለታዎችን መዘከር ለመጪው ትውልድ መሰረት ማኖር ” በሚል መሪ ቃል በታላቅ ክብር ተመረቀ።

ጥቅምት 28/2014 ዓ/ም
የክቡር ሌ/ጄኔራል ወ/ስላሴ በረካ የመታሰቢያ ሀውልት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በጉብርየ ክፍለ ከተማ አደባባይ ተገንብቶ “የምርቃት ስነስርዓት የሀገርና የህዝብ ባለውለታዎችን መዘከር ለመጪው ትውልድ መሰረት ማኖር ” በሚል መሪ ቃል በታላቅ ክብር ተመረቀ።

ጀግናን ማክበር፣ጀግና ማወደስ፣ለጀግኖች ክብር መስጠት ሌላ ጀግና ያፈራል፤ሌ/ጄኔራል ወ/ስላሴ በረካ በጉራጌ ምድር ተፈጥረው ኢትዮጵያን ያኮሩ ኢትዮጵያ ከፍ ያደረጉ የጦር መሪ ዛሬ ዳግም በልጆቻቸው ከፍ ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው እንደገለጹት ክቡር ሌ/ጄኔራል ወ/ስላሴ በረካ በወታደርነት ሙያቸው ከእጩ መኮንነት በመነሳት በተከታታይ ባገኙት የማዕረግ እድገት በኢትዮጵያ ወታደራዊ እድገት ደረጃ በወቅቱ የመጨረሻውን የእድገት እርከን ያገኙ ታላቀ ጀግና ሲሆኑ በልማቱ ደግሞ በዛን ዘመን የማይታመን ታሪክ ሰርዋል፡፡

ዛሬ ብዙ ተቋማት፣ ቴክኖሎጂና ስልጣኔ ባለበት ወቅት ለተፈጠርነው አመራሮች ክቡር ሌተራል ጄነራል ወልደስላሴ በረካ ያደረጉት ሁለገብ ትግል ብዙ ትምህርት የሚሰጡ ጀግና አባት ነበሩ ብለዋል።

አቶ መሀመድ ጀማል አክለውም ጄነራሉ የአመራ ብቃታቸውና ለህብረተሰቡ ያደረጉት የልማት አርበኝነት የአሁኑ ትውልድ በተለይም ወጣቱ መማር አለበት ብለው ወቅቱ የፈጠረልንን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመን በምንችለው ሁሉ ማህበረባችንን ማገዝ አለብን ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የግንባታ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ አቶ ሀብቴ ቸሆ በመድረኩ እንደገለፁት ‹‹የጉራጌ ልማት አባት›› የእኚህ ሰው ሁለገብ ስራ ለወጣቱ በዓርዓያነት የሚታይ ነው ብለዋል፡፡

እኚህ የልማት ጀግና የሚያውቃቸው ብቻ ሳይሆን መጪው ትውልድ ስለታሪካቸው ማወቅ አለበት ያሉት አቶ ሀብቴ ክቡር ሌተራል ጄነራል ወልደስላሴ በረካ መንግስት መስራት አለበት ሳይሉ እና እርዳታ ሳይጠብቁ የህዝቡን አቅም አስተባረው በርካታ ልማቶችን አበርክተዋል ፡፡

አቶ ታምሩ ማኔ የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ እንደተናገሩት ጄነራሉ ከልማቱ ግንባር ቀደም መሪነት በተጨማሪ ህብረተሰቡን በተለይም የጉራጌ አካባቢ ማህበረሰብን በማስተባበርና በአንድ የልማት ድርጅት ጥላ ስር እንዲሰባሰብ በማድረግ የታገሉ የልማት ጀግና መታሰቢያ ሀውልት ከተለያዩ ግለሰዎችና ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከ4.3 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ መገንባት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ያነጋገርናቸው የጄነራሉ ቤሰቦችና አስተያየት ሰጪዎች ሌ/ጄኔራል ወ/ስላሴ በረካ የጉራጌ ብሎም የኢትዮጵያ ጀግና ናቸው ብለዋል።

ከውትድርና ሙያቸው ጎን ለጎን የጉራጌ አጠቃላይ ህብረተሰቡን ለልማት በማስተባር የጉራጌ ህዝብ ራስ አገዝ የልማት ድርጅት በማቋቋም ታላቅ የልማት አርበኛ በመሆን በተለይም በመንገድ፣ በትምህርት፣ በጤናው እና በሌሎች ማህበረሰብ ልማት ላይ ከፍተኛ ስራ የሰሩ ጀግና በዛሬ ትውል እኚህ ጀግና የሚያወድስ ሀውልት በመቆሙ ትልቅ ደስታ እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።

በምርቃት ስነስርአቱ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው፣ የጉራጌ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ባለሀብቶች የፌደራል፣ የክልል፣ የዞን፣ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ከሀገር ውስጥና ሀገር ውጭ ልዩ ልዩ አድናቂዎቻቸው ተገኝዋል።

በመጨረሻም በሌ/ጄኔራል ወ/ስላሴ በረካ ስም የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ቅርንጫፍ በወልቂጤ ከተማ በጉብርየ ክፍለ ከተማ ተሰይሞላቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *