የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ አካባቢዎች አየተዘዋወሩ ማከናወን ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር አገር ማወቅ፣ መተባበርና ወንድማማችነት እንደሚያጠናክር ዶ/ር አለሙ ስሜ ገለጹ።

በጉራጌ ዞን በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ24 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን የአረንጓዴ ልማት የችግኝ ተከላ መካሄዱን ተገለጸ።

የፌደራል የብልጽግና ፓርቲ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚንስትር ዶ/ር አለሙ ሲሜ በታታሪውና በስራ ወዳዱ የጉራጌ ማህበረሰብ በቡታጅራ ከተማ ተገኝተው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ በማካሄዳቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናገሩ።

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ አካባቢዎች አየተዘዋወሩ ማከናወን ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር አገር ማወቅ፣ መተባበርና ወንድማማችነት ያጠናክራል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፓርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዶ ድንቁ እስካሁን በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ24 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል።

በዞኑ በ16 ዘርፎች በተለይም የአረጋውያንና የአቅመ ደካማ ቤቶች አፍርሶ መገንባት፣ የደም ልገሳ፣ የተማሪዎች ማጠናከሪያ ትምህርት፣ የአረንጓዴ ልማት የችግኝ ተከላ፣ በጽዳትና ውበት መሰል ተግባራት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በቀጣይም የክረምት በጎ ፈቃድ ስራ በዞኑ በሁሉም አካባቢ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ አብዶ ድንቁ ገልጸዋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ነስሩ ጀማል ከ6 ሺህ በላይ ወጣቶች በተለያዩ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በማሳተፍ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ለአቅመ ደካሞች አልባሳት ማሰባሰብ፣ የከተማ ጽዳትና ውበት መጠበቅ፣ ደም ልገሳ፣ አረጋዊያን የመንከባከብ መሰል ተግባራት በተሰራው ስራ ከአቻ ከተሞች የተሻለ ውጤት በማስመዝገባቸው እውቅና ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።

በበጎ ፈቃድ የችግኝ ተከላው ላይ ሲሳተፉ ያገኘናቸው ወ/ሪት ሰብሪና ኦርጂኖ እና አቶ መክብብ ማሞ በጋራ በሰጡት አስተያየት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየሄዱ በበጎ ተግባራት ላይ መሳተፍ ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር በአካባቢና በብሄር ከመከፋፈል ይልቅ አባቶቻችን ያወረሱን አንድነታችን እንድናጠናክር ያስችላል ብለዋል።

በዛሬው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ከፌደራል፣ ከደቡብ ክልል፣ በፌደራል ደረጃ የሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆ ድርጅቶችና ሲቪል ማህበራት ከጉልባማ፣ ከጉራጌ ዞንና ከቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች፣ ከመምህራን ማህበር ፣ የዞንና ከከተማው የወጣቾች ዘርፍ ኃላፊዎች ባለሙያዎችና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *