የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች የተለያዩ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች እያከናወኑ መሆኑም በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ሀምሌ 16/2014 ዓ.ም

የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች የተለያዩ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች እያከናወኑ መሆኑም በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በወረዳዉ የአቅመ ደካሞችና የዘማች ቤተሰብ ማሳዎች የማረስና በዘር የመሸፈን ስራ መሰራቱም ተጠቁሟል።

በተለያዩ አካባቢዎች 1 ሚሊየን 2 መቶ ሺህ የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞች ተተክለዉ እንዲጸድቁ የእንክብካቤ ስራ እየተሰራ ነዉ።

የአበሽጌ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ የሱፍ አብድልሰመድ እንዳሉት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች የተለያዩ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች እየተሰራ ነዉ።

በወረዳዉ በተለያዩ የልማት ዘርፎች 9 ሺህ 6 መቶ 20 ወጣቶች በበጎ ፍቃድ ስራዉ እየተሳተፉ እንደሆነም ተናግረዋል።

የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ፣ የማህበረሰብ መጸዳጃ ቤት ፣ዉሃ ያቆሩ ቦዮች እንዲያፋስሱ የማድረግ ስራ ፣ የደም ልገሳ እንዲሁም የጋራ መጸዳ ቤት ግንባታ ፣ በኤች አይ ቪ ኤድስ ዙሪያ ግንዛቤ የመስጠት ስራና በበርካታ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ ተግባራት እያከናወኑ መሆኑም አብራርተዋል።

በሁሉም አካባቢዎች ችግኝ የመትከልና እንዲጸድቁ የእንክብካቤ ስራዎች በስፋት እየተሰራበት እንደሆነም አስረድተዋል።

የ4 አቅመ ደካሞች ቤት አዲስ ግንባታና 9 ነባር ቤቶች የጥገና ስራ ፣ የዘማች ቤተሰብ ማሳቸዉ በማረስና ዘር በመዝራት እና የአረም የማረምና ፣ የዉስጥ ለዉስጥ መንገድ የማስፋት ስራ የድልድይ ጥገናና አዳዲስ ድልድይ ግንባታና ማዕድ የማጋራት በሌሎችም ስራዎች ላይ ወጣቶች አርአያነት ያለዉ ስራ እየሰሩ እንደሆነም አስረድተዉ

ወጣቶች በሰላም ዕሴት ግንባታ ፣ በሰላም መስፈንና ወጣቶች ተደራጅተዉ አካባቢያቸዉን እንዲጠብቁ እንዲሁም በስነ ምግባር እንዲታነጹ የማድረግ ስራም እየተሰራ እንደሆነም አብራርተዋል።

በወረዳዉ በዘንድሮ አመት በክረምት በጎ ፍቃድ ወጣቶች እስካሁን የተሰሩ የተለያዩ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ ተግባራት በገንዘብ ሲተመን 1 ሚሊየን 470 ሺህ 350 ብር እንደሚገመትም አስረድተዋል።

ወጣቶች የጀመሩትን በጎ ተግባር የበለጠ አጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉ ኃላፊዉ አሳስበዋል።

በቁሊት አንድ ቀበሌ ቤት ከተሰራላቸዉ አረጋዉያን መካከል ወይዘሮ ወርቄ አባቡ እንዳሉት ቀደም ሲል ይኖሩበት የነበረዉ ቤት በላያቸዉ ሊፈርስ እንደነበረና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ይህንን ችግር ተገንዝበዉ አፍርሰዉ ስለሰሩላቸዉ ደስተኛ መሆናቸዉም ተናግረዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

መረጃዎቻችበተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *