የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ሙስጠፋ ኢሳ እና የቢሮው ምክትል ኃላፊዎች ከተቋሙ ስራተኞች ጋር ትውውቅ በማድረግ በዛሬው እለት ስራቸው በይፋ ጀምረዋል።


የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ሙስጠፋ ኢሳ እና የቢሮው ምክትል ኃላፊዎች ከተቋሙ ስራተኞች ጋር ትውውቅ በማድረግ በዛሬው እለት ስራቸው በይፋ ጀምረዋል።

በዚሁ መሰረት አዲሶቹ የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሃላፊዎች የስራ ትውውቅ ያደረጉ ሲሆን በእለቱም በ2016 ዓ.ም የተከናወኑ ስራዎች ተገምግመው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በቅርቡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በሰጡት የአመራር ምደባና ሽግሽግ መሰረት፦

1,አቶ ሙስጠፋ ኢሳ አብድላ የማእከላዊ ኢትዩጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሃላፊ።

2 ,አቶ እሸቱ ተሾመ ወዬሳ :-በምክትል ሀላፊ ማዕረግ የቢሮው ሀላፊ አማካሪ።

3 ,አቶ ተመስገን ሀይሌ ፈይሳ፦ምክትል ቢሮ ኃላፊና የገጠር ስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ።

4 , ወ/ሮ ዙልፋ አለዊ ነጋሽ ፦ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የአነስተኛ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንድስትሪ ልማት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

በዚሁ መሰረት አዲሶቹ አመራሮች ከተቋሙ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር ትውውቅ እና መስሪያ ቤቱን የጎበኙ ሲሆን በዚሁ ወቅት አዲሶቹ አመራሮች በዘርፉ ተልዕኮዎችና አጠቃላይ ስራዎች ዙሪያ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

በእለቱም በ2016 ዓ.ም የተከናወኑ የተቋሙ ስራዎች ተገምግሞ በቀጣይ የ2017 ዓ.ም እቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *