የካይዘን አሰራር ተግባራዊ በማድረግ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ አስታወቀ።

ሰኔ

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንደገለጹት መምሪያው የካይዘን አሰራር ተግባራዊ በማድረግ ተቋሙ ለስልጠና፣ ለቪዲዮ ኮንፈረንስ እና ሌሎች አገልግሎቶች ምቹና ማራኪ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።

ተቋሙ 3መቶ ሺህ ብር ወጪ በማድረግ የካይዘን አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ የመምሪያው ባለሞያዎች ከወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመሆን የስልጠናና የቪዲዮ ኮንፈረንስ ክፍል ሳቢና ምቹ የማድረግ ስራ መሰራቱንም ተናግረዋል።

የሴክተሩ ባለሙያዎች ከኮሌጅ ጋር በመተባበር የካይዘን አሰራር እንዲሰሩና በቀጣይ በሌሎችም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ስልጠና ተሰጥቶ ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል።

በቀጣይም የካይዘን አሰራር በመንግስት መስሪያ ቤት ተግባራዊ በማድረግ ለተገልጋዮችና ለሰራተኞች ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር እንደሚሰራ ኃላፊው ተናግረዋል።

በተያያዘ መምሪያው የባለሙያ አቅም አሟጦ ለመጠቀም የተለያዩ ግብዓት ለማሟለት ጥረት እየተደረገ ሲሆን በበጀት አመቱ ለአቶ ሸለመ አርጋው ለአካል ጉዳተኞች አገልግሎት የሚውል በ169 ሺህ ብር ሞተር ተገዝቶ እንደቀረበላቸው ተናግረዋል።

በመሆኑም አቶ ሸለሙ በተሽከርካሪ እጦት ምክንያት የእለት ተዕለት እብቅስቃሴያቸው እንዳይስተጓጉልና ቢሮ በሰዓቱ ተገኝተው ስራቸውን በተገቢው እንዲሰሩ ያስችላቸዋል ብለዋል።

ይህ በጎ ተግባር በማስፋት አካል ጉዳተኞች በተገቢው ተግባራቸውን እንዲከውኑና የእኩልነት ስሜት እንዲሰማቸ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባልም ብለዋል።

በጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምርያ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሸለመ አርጋው መምሪያው የሞተር ተሽከርካሪ ግዢ ፈጽሞ ማቅረብ በመቻሉ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

እንደ አቶ ሸለመ ገለጻ የመኖሪያ ቦታቸው አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሳ በዊልቸር ተንቀሳቅሶ በሰአቱ ቢሮ ተገኝተው ስራቸው በተገቢው ለመከወን ይቸገሩ ነበር።

የተሽከርካሪ ችግር በመቀረፉ በሰዓቱ ቢሮ በመገኘት ውጤታማ ስራ ለመስራት እንደሚያግዛቸው ጠቁመው መምሪያው ላደረገላቸው በጎ ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

የመምሪያው ሰራተኞች በበኩላቸው ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የተጀመረው የካይዘን አተገባበር ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

በቀጣይ ያላቸው እውቀትና ጊዜ ተጠቅመው ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚሰሩ የገለጹት ሰራተኞቹ ያላቸው ልምድ በመጠቀም በሌሎች የመንግስት ተቋማት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

መምሪያው ለአቶ ሸለመ ገዝቶ ያበረከተለትን ሞተር የቁልፍ እርክክብ ተደርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *