የከተማ ግብርና ስራዎች በማጠናከር በወተት ምርት አቅርቦት ፣በዶሮ እርባታ፣ በእንስሳት እርባታ ፣በአትክልትና ፍራፍሬና በሌሎችም ምርቶች የተመዘገቡ ውጤቶች ማስፋት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ ።

በወልቂጤ ከተማ እየተሰሩ ያሉ የሌማት ትሩፋቶች የዞንና የከተማዉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ በተለያዩ የከተማ ግብርና ዘርፎች የተሰማሩ አካላትና የህዝብ ምክር ቤት አባላት ተዛዙረዉ ጎብኝተዋል።

በሌማት ትሩፋት ጉብኝት ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት በከተሞች አካባቢ የሌማት ትሩፋት ከየትኛዉም አካባቢ ባልተናነሰ መልኩ ጠንካራ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

ስራ አጥ ወጣቶች ተደራጅተዉ በዶሮ እርባታ ፣በእንስሳት እርባታ ፣የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎች መሰረት ያደረገ ስራ እየተሰራ መሆኑም ያየንበት ጉብኝት ነዉ ብለዋል።

በአንድ የወተት ላም በቀን እስከ 35 ሊትር ማግኘት የሚችሉ እንዲሁም አቶ ዘሪሁን ኸሊል በግላቸው እስከ 45 የወተት ከብቶች በማርባት ዉጤታማ ስራ እየሰሩ መሆናቸውን በመስክ ምልከታቸዉ መመልከትና መቻላቸው ተናግረዋል።

ከዚህም ባለፈ በአትክልትና ፍራፍሬ በተለይም በፖፖያና በቲማቲም ልማት ስራዎች ተሰማርተዉ የሚገኙ ወጣቶች የአካባቢዉን ገበያ ለማረጋጋት አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሆነም አመላክተዋል።

የከተማ ግብርና ዘርፍ አዋጭ እንደሆነም ተናግረዉ ለነዚህም ሙያዊ ድጋፍና ክትትል ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበትም አስረድተዉ በተለይ የእንስሳት ህክምና በላብራቶሪ የተደገፈ እንክብካቤና ህክምና እንዲሁም የእንስሳት አዳቃይ ቴክኒሻኖች እጥረት እንዳለም አመላክተዋል።

ማህበራቶች በተሰማሩበት ዘርፍ ከቦታ አቅርቦት ችግር ያነሱትን ዉስንነት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚቀርፍም አብራርተዋል።

የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታዉ በሌማት ቱሩፋት ጉብኝቱ ተገኘተዉ እንዳሉት የከተማ ግብርና ለማዘመን ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል።

በዶሮ እርባታ ፣በከብት ድለባ ፣በወተት ምርት ፣ ቲማቲም አቦካዶ ጎመን መሰል የጓሮ አትክልቶች እየተመረቱ ይገኛሉ ብለዉ የእንስሳት ምርት ለማሻሻልና የወተት ምርት ለማሳደግ በሲክኖራይዜሽን የማዳቀል ስራ በመስራት በዚህም ተጨባጭ ዉጤት እየመጣ ይገኛል።

በከተማዉ የወተት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በቀን በአንድ የወተት ላም ከ38 እስከ 50 ሊትር ወተት እንደሚታለብም አመላክተዉ በዚህም በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ዉጤታማ ስራ እየሰሩ እንደሆነም አብራርተዋል።

በከተማዉ ደረጃ የምግብ አቅርቦት ችግር በማሻሻልና ከተማዉ ማዘመን ፣ በቂ ምግብ ማግኘት እንዲቻል የከተማ ግብር ማዘመን እንደሚገባም ተናግረዉ በከተማ በተለያዩ ግብርና ዘርፎች የተሰማሩ አካላት ከመሬት ጥበት ጋር ያነሱትን ችግር ለመቅረፍ መንግስት በትኩረት እንደሚሰራበትም አብራርተዋል።

የስጋ ፣ የእንቁላልና የወተት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የባለሙያተኞች የእዉቀት ችግር በስልጠና እንዲታገዝ በማድረግና በተገቢዉ ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸዉ ዉጤታማ ስራ እንደሚሰራም አመላክተዋል።

ተዛዙረዉ የጎበኟቸዉ የሌማት ትሩፋት ስራዎች የበለጠ በማስፋት የተሻለ ስራ መስራት እንደሚቻል የሚያሳይ እንደሆነም አመላክተዋል።

ወጣቶች ጊዜያቸዉን አለባሌ ቦታ ከመዋል ወጥተዉ በነዚህና መሰል የግብርና ስራዎች በመሰማራት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸዉን ማረጋገጥ እንዳለባቸዉም አአስረድተዉ በ33 ማህበራት ከ6 መቶ በላይ ስራ አጥ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሆነም አብራርተዋል።

የወልቂጤ ከተማ ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ወልደማሪያም ዘሬ እንዳሉት በከተማ ግብርና ስራዎች ላይ ከፍተኛ ዉጤት እየመጣ እንደሆነና በዚህም ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት ዉጤታማ እየሆኑ እንደሆነም ተናግረዋል።

ቀደም ሲል ከወሊሶ ይገባ የነበረዉን የወተት ምርት አሁን ላይ መቅረፍ እንደተቻለም አንስተዉ በከተማዉ በወተት ምርት ወደ 33 ማህበራት ተደራጅተዉ እየሰሩ እንደሆነና የአካባቢዉ የወተት ምርት አቅርቦት መቅረፍ ችለዋል ብለዋል።

በአዲስ ክፍለ ከተማ በወተት ላም ምርት የተሰማራዉ አቶ ዘሪሁን ህሊል እንደሚለዉ በከተማዉ16 የወተት ማከፋፈያዎች በተለያዩ ቦታዎች በመክፈት ለማህበረሰቡ ወተት እያቀረበ እንደሀነም አስረድተዋል።

በሁለት ከብት የወተት ምርት ስራ የጀመረዉ አቶ ዘሪሁን አሁን ላይ ወደ 46 የወተት ከብቶች ማድረስ እንደቻለና ከነዚህም ዉስጥ 31ላሞች የሚታለቡ እንደሆነም ተናግረዉ በዚህም የወተት ምርት ስራ ለ8 ሰዎች የስራ ዕድል እንደፈጠረላቸዉም አመላክተዋል።

ዉጤታማ ስራ እንዲሰራ መንግስት የሚያደርግለት ድጋፍና ክትትል የበለጠ አጠናክረዉ መቀጠል እንዳለበትም ተናግሮ በተሰማራበት የወተት ምርት ዉጤታማ ስራ እንዲሰራ የመሬት ጥበት እንዳለበትና ይህንንም መንግስት እንዲቀርፍለትም ጠይቋል።

በጉብሬ ክፍለ ከተማ አንቸነ ይተንሸ ማህበር አቶ ጸበሉ ትግስቱ እንዳሉት በመጀመሪያ ማህበራቸዉ በደረቅ እንጀራ አቅርቦት ተሰማርተዉ የነበረና አሁን ላይ በክፍለ ከተማዉ የሚስተዋለዉን የወተት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በወተት ከብት እርባታ ተሰማርተዉ እየሰሩ እንደሀነም አመላክተዋል።

ሌላዉ በጉብሬ ክፍለ ከተማ የቸዋችመነ ማህበራት የፖፖያ ምርጥ ዘር ችግኝ በማፍላት ለማህበረሰብ እያቀረቡ እንደሆነና ከዚህም ጎን ለጎን የዶሮ እርባታ ሰራ እየሰሩ እንደሆነም ተናግረዋል።

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Tiwter https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *