የከተማ አስተዳደሩ ከጣጤሳ ጥልቅ ጉድጓድ ወደ ከተማው ለማድረስ ለሚዘረጋው የውሃ መስመር ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ዝርጋታውን ከሚያከናውነው ድርጅት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ!!

የወልቂጤ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ እንዳለ ገብረመስቀል የውል ስምምነቱ በተፈራረሙበት ወቅት ተናግረዋል።

ችግሩን ይቀርፋል ተብሎ ከተያዙ ዕቅዶች አንዱ ጣጤሳ ላይ ሁለት ጥልቅ ጉድጓዶች ማስቆፈር ነበር ያሉት ከንቲባው የቁፋሮ ስራው ተጠናቆ አሁን ላይ የዝርጋታ ስራ ብቻ መቅረቱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከተማ አስተዳደሩ ጉብሬ ክፍለ ከተማ በብልሽት ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቁሞ የነበረው ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁንና በክፍለ ከተማው ለሊዝ መንደር በ UIIDP በተገኘ 3 ሚሊዮን ብር የውሃ መስመር ለመዘርጋት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ሔኖክ አብድልሰመድ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የከተማው የውሃ ስርጭት ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የመስመር ዝርጋታውን ለማስጀመር ጳውሎስ አበበ ጠቅላላ ውሃ ስራ ተቋራጭ ከተባለው ድርጅት ጋር የውል ስምምነት የተደረገበት የጣጤሳ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ማሳያ መሆኑንም አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈ በዘርፉ ያሉ የአሰራር ችግሮችን በመቅረፍ የከተማው ማህበረሰብ በፍትሃዊነት ውሃ እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል።

የጳውሎስ አበበ ጠቅላላ ውሃ ስራ ተቋራጭ ድርጅት አቶ ጳውሎስ አበበ በበኩላቸው የዝርጋታውን ስራ በሁለት ወራት በማጠናቀቅ ለማስረከብ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሮቤል ሸንቁጤ እንዳሉት በከተማው የሚስተዋለውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ጽህፈት ቤቱ ከከተማ አስተዳደርና ከዞን ጋር በመሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ጣጤሳ ላይ ለተቆፈረው የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ተገቢ ክፍያ ወጪ መደረጉን ጠቅሰው በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ለመስመር ዝርጋታ ስራ የ31 ሚሊዮን 8 መቶ 92 ሺህ 55 ብር የውል ስምምነት መደረጉን ገልጸዋል።

የተበላሹ የውሃ መስመሮችን በአዲስ የመተካትና ዝርጋታው ያልነበሩ አካባቢዎችንም የውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አቶ ሮቤል መናገራቸው ከከተማው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *