የእኖር የመስቀል በዓል ዝግጅት ድባብ
“ኧሽረኘ/ኧሽርሽርት ገያ” የበዓል ዋዜማ ( ጉንችሬ ገበያ ) ፦

መስከረም 13/2015 ዓ.ም

የእኖር የመስቀል በዓል ዝግጅት ድባብ
“ኧሽረኘ/ኧሽርሽርት ገያ” የበዓል ዋዜማ ( ጉንችሬ ገበያ ) ፦

“ኧሽርሽርት/ኧሽረኘ ገያ” የተባለውም በዋናነት በጉራጌ ብሔረሰብ ዘንድ ከሚከበሩ ታላላቅ በዓላት (ከአረፋና ከመስቀል) ግብይት ስርዓትና ባህርይ ጋር በመነሳት የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡

የሻጭና የገዢው ትርምስ፣ ሁካታና ጫጫታ፣እርስ በርስ ማጉረምረም፣ በሀሳብ መዋለልና መመሰጥ፣ወከባ፣ ግፈያና ሽመያም የተለመደ ነው፡፡

“ኧሽርሽርት ገያ” የፈለጉትን ለማግኘት ሌላ አማራጭ የገበያ ቀን የሌለው( የበዓል ዋዜማ ገበያ )እንደመሆኑ መጠን በዕለቱ የማይሸጥና የማይለወጥ ነገር የለም፡፡

ዓመቱን ሙሉ በልዩ ሁኔታ ሲቀለብ የነበረ ሰንጋ፣ ቆጮ፣ ቅቤ፣ ማር፣ ቅመማ ቅመምና ሌሎችም የምግብና የማስዋቢያ ቁሳቁሶች ገበያ ውስጥ ይገኛሉ።

በእኖር ወረዳ ረቡዕ (ኧገዜና ጋዝአንቸ ገበያ)፣ሰኞና ዓርብ (ጉንችሬ ገበያ) እንዲሁም ቅዳሜ (ጋዝአንቸ ገበያ) ታዋቂ ናቸው፡፡

በዓል ሲቃረብ እነዚህ ገበያዎች ከወትሮ በተለየ ይዘትና ስፋት ከተለመደው ሰዓት አስቀድመው ገና በጠዋቱ ግብይት ይጀምራሉ፡፡

በዚህም ምክንያት የእብደት ገበያው በሚሸምቱ ሰዎች፣ ለገበያ በሚቀርቡ እንስሳት እንዲሁም ሌሎች ምርቶች ይጥለቀለቃል።

የእብደት ገበያ በዓመት አንዴ የሚመጣ ገበያ እንደመሆኑ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ካልገጠመ በቀር ሁሉም ሰው እንዳያመልጠው አይፈልግም።

ዛሬ ዓርብ ጉንችሬ የመጨረሻው የመስቀል በዓል “የሽርሽርት ገያ” ግብይትን እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ጋንዛቸ ደግሞ በነገው እለት ቅዳሜ የመጨረሻውን “የሽረኘ ገያ ” ገበያተኞች ተቀብላ ታስተናግዳለች፡፡

እነዚህ ገበያዎች የህብረተሰቡ ማህበራዊ ኑሮን ለማጠናከርና የወረዳውን ገቢ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ፡፡
በቀጣይም የቱሪስት መስህብ እንዲሆኑ የማስተዋወቅ ስራ በመስራት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት ይገባል ሲል የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን ዘግቦታል።

✍ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የመስቀል በዓል ተመኘን፡፡
ወሔ ሙርኣ !! ወሔ ወኸመያ ኧህርነሁዋ!!!

ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *