የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 38ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2017 በጀት አመት የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ማስፈሚያ 253 ሚሊዮን 89 ሺህ 538 ብር በጀት አፀደቀ።

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችን አፅድቋል በዚህም መሰረት የወረዳው ዋና አስተዳደሪ እጩ በጉራጌ ዞን ም/ል አስተዳደር በአቶ አበራ ወንድሙ ለም/ቤቱ ቀርቦ አቶ አሰበ ካብቱ እንዲሆኑ በሙሉ ድምፅ የወረዳው ዋና አስዳዳሪ ሆነው እንዲመሩ ተሹመዋል።

በመቀጠልም የወረዳው ዋና አስተዳደሪ አቶ አሰበ ካብቱ 3 እጩዎች ለም/ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን ÷
1,አቶ ትምህርቱ ኧርዳ የእኖር ኤነር መገር ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ
2, አቶ ካሳሁን ተክሌ የወረዳው ረዳት የመንግስት ተጠሪና የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ
3, ወ/ሮ ሰሚራ መንሱር የወረዳው ረዳት የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ሆነው እንዲያገለግሎ በሙሉ ድምፅ ሹመታቸው ፀድቋል።

ምንጭ:- የወረዳው መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *