በጉራጌ ዞን በእምድብር ከተማ አስተዳደር በበጀት አመቱ ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ።
የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ የጉራጌ ማህበረሰብ በሌሎች አካቢዎች ልማትን በማፋጠን ከተሞች እንዲለሙ ያደርጋል።
አክለውም የጉራጌ ማህበረሰብ ወደ ገጠርቱ ሲገባ በውብ ጀፎረ፣ በአካባቢው ጽዳት እና ጥበቃ ፣በቤት አሰራሩ ለሌሎች ልምድ የሚወሰድበት ህዝብ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም እነዚህ ስራዎች ወደ ዞኑ ማምጣት ያስፈልጋል ያሉት አቶ አበራ የዞኑ ከተሞች ይበልጥ በማልማት የጉራጌን ማህበረሰብ የሚመጥኑ መሆን አለባቸው ብለዋል።
ከእነዚህም እምድብር ከተማ ውብ ፤ ማራኪ እና ለኑሮ አመቺ እንዲሆትሆን እንዲሁም በከተማ ግብርና የሚሰሩ የልማት ስራዎች እጅግ አመርቂ በመሆናቸው አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት ውድማ በበኩላቸው በጉራጌ ዞን የህብረተሰቡ እና የመንግስት አቅም በማቀናጀት በተሰሩ ስራዎች በርካታ ለውጦች የታዩ ቢሆንም የጉራጌ ከተሞች ግን ጉራጌን የሚገልጹ ባለመሆናቸው በቀጣይ ብዙ መስራት እንደሚገባ አስታውቀዋል።
ከተሞች የሚለወጡት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ሲታከልበት ነው ያሉት አቶ ታምራት በእምድብር ከተማ ብሎም በዞናችን ከተሞች በህብረተሰቡ እና በመንግስት የተጀማመሩ ቅንጅታዊ ስራዎች ይበልጥ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
የእምድብር ከተማ ከንቲባ አቶ ግምባሩ በርጋ እንደገለፁት ከተማዋ የፈርጅ ሶስትነት ደረጃ ከአገኘች ጊዜ ጀምሮ በሚሰሩ ልማቶች የህብረተሰቡ የልማት ፍላጎት በማሟላት የመልካም ችግሮችን መቅረፍ ተችሏል።
ከእነዚህም የመብራት ዝርጋታ፣የዲችና የኮብል ንጣፍ፣የመንገድ ከፈታ፣የጠጠር ንጣፍ፣የአረንጓዴ ማልበስ፣ከተማዋ ማስፋት እና በቂ የመኖርያ ቤት ግንባታ እና የኢንቨስትመንት መሬት ማዘጋጀት መቻሉ ተናግሯል።
በከተማው በተሰሩ ስራዎች ውጤት በማምጣት በሌሎች ልምድ ልውውጥ እየተደረገ እንደሆነ የገለፁት አቶ ግምባሩ ዘንድሮ ተዘጋጅቶ በነበረው ሀገር አቀፍ የከተሞች ፎረም የ3ኛ ደረጃ በመውጣት ተሸላሚ መሆኑን አስታውሰዋል።
በከተማው በሚሰሩ ስራዎች የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ እና ለብዙ ወጣቶች የስራ እድል እየፈጠሩ መሆኑን አክለዋል።
የእምድብር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስከያጅ አቶ ሲሳይ ተክሌ እንደገለፁት በበጀት አመቱ በማቺንግ ፈንድ እና በውስጥ ገቢ ተሰርተው ዛሬ ከተመረቁት የኮብል ሳይት ፣ዲቾች፣የአዳራሽ አጥር፣የቄራ ጥገና እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ገልጸዋል።
እነዚህም 16 ሚሊየን 3መቶ 27 ሺ 482 ብር ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን በቀጣይ የከተማዋ መልሶ ማልማት ላይም በትኩረት እንደሚሰራበት ተናግረዋል።
አቶ ሲሳይ አክለውም በዞንና በክልል ደረጃ የሚጸድቁ የካፒታልና የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ጸድቀው ወደ ስራ እንዲገቡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራበት በመጠቆም።
ከተማዋ በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ እንድትሆን እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ሲሳይ ለማህበራ፣ ለኢንቨስትመንት ፣ከመከላከያ ሰራዊት ለተመለሱና ለሊዝ ጫረታ የሚሆኑ መሬቶች አዘጋጅቶ መስጠት መቻሉ አመላክቷል።
አቶ ዋቄ ባንቆ እና አቶ ወርቁ ሸዋ የእምድብር ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ሲሆኑ የከተማው ማህበረሰብ ከተማዋ የፈርጅ ሶስትነት ደረጃ እንድታገኝ ከማድረግ ጀምሮ በገንዘብ፣በጉልበትና በእውቀት እያገዘ እንደሆነ አስታውቀዋል።
በህብረተሰቡና በመንግስት ቅንጅት ከተማዋ በየ ጊዜው የእድገት ለውጥ እያመጣች እንደሆነ ተናግረው ቀጣይም ድጋፋቸው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም በከተማው እድገት ንቁ ተሳትፎ ለሚያደርጉ አካላት የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።