የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጤና አገልግሎትና ተደራሽነት ለማሳደግ እየሰራች ያለውን ተግባር ለማጠናከር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

ቤተክርስቲያኒቱ በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ ከ49 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ያስገነባችው የዌሬ ቅዱስ ማርቆስ ጤና ጣቢያ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእምድብር ሀገረ ስብከት በዞኑ የትምህርት ፣ የውሃና፣የጤና፣ የመንገድና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች በማስፋፋት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገች ትገኛለች ብለዋል።

እንደ ምክትል አስተዳዳሪው ገለፃ መንግስት ለዜጎች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያልደረሰባቸው በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች በመኖራቸው ቤተክርስቲያኒቱ በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች የመሰረተ ልማት ችግሮቻቸው ለመፍታት የጀመረችው በጎ ተግባር አጠናክራ መቀጠል አለባት ብለዋል።

የዞኑ አስተዳደር ደግሞ በቀጣይ ቤተክርስቲያኒቱ የምታከናውናቸው የልማት ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግም ምክትል አስተዳዳሪ ገልጸዋል ።

ለምረቃ የበቃው የዌሬ ቅዱስ ማርቆስ ካቶሊክ ጤና ጣቢያ ከአካባቢው ማህበረሰብ ባለፈ ለሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ጭምር አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን የፕሮጀክቱን የግንባታ ወጪ ለሸፈነችው ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምስጋና አቅርበዋል።

የቸሃ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙራድ ከድር በበኩላቸው ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ባለፉት አመታት የወረዳው ማህበረሰብ የመሰረተ ልማት ችግሮች በመፍታት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገች የእምነት ተቋም እንደሆነች ገልጸዋል።

በወረዳው የሚስተዋለው የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር በመቅረፍ ህብረተሰቡ የግልና የአካባቢው ንጽህና ከመጠበቅ ባሻገር ከውሃ ወለድ በሽታ እንዲጠበቅ የሰራችው ስራ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

ለምረቃ የበቃው የዌሬ ቅዱስ ማርቆስ ካቶሊክ ጤና ጣቢያ ደረጃውን የጠበቀና ከ16 ሺህ በላይ የወረዳውና የአጎራባች ወረዳ የህብረተሰብ ክፍሎች ማስተናገድ እንደሚችል ገልጸዋል።

ጤና ጣቢያውን ዘመኑን በሚመጥን ደረጃ የተገነባ ሲሆን ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲችል የወረዳው አስተዳደር ድጋፍ እንደሚያደርግ አቶ ሙራድ ገልጸዋል።
የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የምትሰራቸው የልማት ስራዎች ለሌሎች የእምነት ተቋማት አርአያ ናት ብለዋል።

ጤና ጣቢያው ህብረተሰቡ በሚፈልገው ደረጃ አገልግሎት እንዲሰጥ በማስቻል በተለይም የእናቶችና የጨቅላ ህፃናትን ሞት ከመቀነስ እና ሌሎችም አገልግሎቶች በጥራት ለመስጠት በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር አባ ተሾመ ፍቅሬ የዌሬ ቅዱስ ማርቆስ ካቶሊክ ጤና ጣቢያ ግንባታ ወጪው ከ49 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን ወጪው የተገኘው ጣሊያን ሀገር ከሚገኘው ከወርልድ ዶክተርስ ሲሆን ሌሎች የአካባቢው ተወላጆች እና የዞኑ አስተዳደር ድጋፍ አድርገዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ጤና ጣቢያውን አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ጤናማና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የአካባቢው ህብረተሰብ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠው እንሄዱ ጊዜ፣ገንዘብና ጉልበታቸው ይባክን እንደነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል ።

ይህ ደረጃውን የጠበቀ ጤና ጣቢያ መገንባቱ ከነዚህ ችግሮች ሁሉ እንደሚያድናቸው ገልፀው ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጥ ፣ስፈላጊውን ጥበቃ እንደሚያደርጉለት ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል።

በምርቃት ስነስርአቱ በየደረጃው የሚገኙ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የስራ ሀላፊዎችና የሀይማኖት አባቶች፣የዞንና ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ደናግላንና የጤና ባለሙያዎች፣የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን በግንባታው ሂደት አስተፅኦ ያበረከቱ አካላትና የረጂ ድርጅቱ ተወካዮች የእውቅና ሽልማትና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ስለምትከታተሉ እናመሰግናለን!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *