የአዳብና ባህል ፌስቲቫል በጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ በኬላ ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎች በልዩ በድምቀት ተከበረ።

መስከረም 22/2015 ዓ/ም

የአዳብና ባህል ፌስቲቫል በጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ በኬላ ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎች በልዩ በድምቀት ተከበረ።

በዓሉ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ ለትውልድ ተሻጋሪ እንዲህን የሁሉም ባለድርሻ አከላት የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የወረዳው ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት አስታውቋል።

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቀለመወርቅ ሺመክት እንደገለፁት የአዳብና ባህላዊ ፌስቲቫል ከጥንት ጀምሮ በሶዶ ቤተ ጉራጌ ዘንድ በታዳጊ ወጣቶችና ልጃገረዶች በልዩ ድምቀት እየተከበረ እስከ ዛሬ ደርሷል።

በዚህ ባህላዊ ጫወታ ከወረዳ ከተለያዩ ቀበሌዎች የተውጣጡ ወጣት ሴቶችና ወንዶች የተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎች በመጨፈር በነፃነት ይዝናናሉ።

በዓሉም ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት 5 ድረስ በተመረጡ ቦታዎች የአበቤ፣ዪቦላላና ሌሎች ባህላዊ ዜማዎች በመጫወት እንዲሁም የአጋቲ ወይም የተከሻ ዝላይ ፣ የእንሰራ መስበር፣የገመድ ዝላይና ሌሎች ባህላዊ ትዕይንቶች ይካሄዳሉ።

በተለይም ወጣት ሴቶች በልዩ ፀጉር አሰራር ፣በውብ ባህላዊ አልባሳትና በአደይ አበባ ተጊጠው የሚታዩበትና ወንዱም አይኑ ያረፈባትን መርጦ ሎሚ የሚወረዉርበት በመሆኑ አዳብና የጋብቻ መሰረት እንደሆነም ይታመናል ብለዋል።

በዓሉ ባህላዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ በማልማትና በማስተዋወቅ ሳይበረዝ ለትውልድ እንዲተላፍ የባህሉ ባለቤት ከሆነው ማህበረሰብ፣የመንግስት አካላትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት እንደሚሰራ ገልፀዋል ።

የወረዳዉ የመንግስት ኮመኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምገስ አባይ በበኩላቸው የአዳብና ፌስቲቫል በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቁ ስፍራ ከሚሰጠው የመስቀል በዓል ተከትሎ የሚከበር በመሆኑ ለመስቀል በዓል ከተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የመጡ የአካባቢው ተወላጆችና ሌሎችም አንግዶች ይሳተፉበታል ብለዋል።

በዘንድሮው አዳብና ካለማንም ቀስቃሽ በመጡ ከ20 ሺ በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይ ልጃገረዶችና ወጣቶች መከበሩን የገለፁት አቶ ሞገስ አዳብና ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ ሳይበረዝ ለትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆን ጽህፈት ቤቱ ከወረዳው አሰተዳደርና ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ጋር በመሆን ባህሉን የማስታወቅ ስራ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ይህም የአዳብና ክብረ በአል ቱሪስቶችን በተሻለ መልኩ በመሳብ ከማህበራዊ ፍይዳው ባሻገር ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዲሩት ያደርገዋል ብለዋል።

አዳብና ባህላዊ ጨዋታ ላይ አግኝተን ከነጋገርናቸዉ ወጣቶች መካከል ወጣት ቤቴሌሄም አንዳርጌ፣ ፣ሄናክ አድማሱ ፣የም ኢፋ በሰጡት አስተያየት አዳብና ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በነፃነት በመጫወት የሚደሰትበት ልዩ ቀን ነው።

በተለይም የትዳር አቻቸውን ሎሚ በመወርወር፣ ማስቲካና መሠል ሶጦታዎችን በመስጠት ከመረጡ በኋላ የቤተሰቦቻቸው ምክክር ታክሎበት ለትዳር የሚተጫጩበት ልዩ ትርጉም አለው ብለዋል።

ባህላዊ ይዘቱን ተጠብቆ እንዲሄድ በሚደረገው ጥረትም ወጣቹ የጎላ ሚናቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው።
ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *