የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ሰልጠና ለመምህራንና ለርዕሰ መምህራን መሰጠቱን የተማሪዎች የዉጤት ስብራት ለማሻሻል ፋይዳዉ የጎላ መሆኑም የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

የዞኑ ትምህርት መምሪያና የዞኑ መምህራን ማህበር ባለድርሻ አካላቶች በጋራ በመሆን የስልጠና አሰጣጡ በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ መስተዳደሮች ተዛዙረዉ ተመልክተዋል።

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም በተለያዩ የስልጠና ማዕከላት ተዛዙረዉ በጎበኙበት ወቅት እንዳሉት በሁሉም አካባቢዎች የ2ኛ ደረጃ መምህራን ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች 2ኛዉ ዙር በአዲሱ ስርዓት ትምህርትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስልጠና እየተሰጠ ነዉ።

በዚህም በ69 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተዉጣጡ ከ1 ሺህ 2 መቶ 69 መምህራን፣ ርዕሰ መምሀራንና ሱፐርቫይዘሮች በ41 የስልጠና ጣቢያዎች ስልጠና እየወሰዱ እንደሆነም አመላክተዋል።

ሰልጣኞች በአዲሱትም/ት ትውውቅ፣በፈተና እቅድ ዝግጅት እና በክፍል ዉስጥ መማር ማስተማር አመራር ትኩረት ያደረገ ስልጠና መሰጠቱ በተማሪዎች የሚስተዋለዉን የዉጤት ስብራት ይቀይረዋል ብለዋል።

ለመምህራን ግንዛቤ መፍጠሩ በቀጣይ በእዉቀትና በስነ- ምግባር የዳበረ ትዉልድ ለመፍጠር የሚያግዝ እንደሆነም አብራርተዋል።

ባለፉት ሁለት አመታት በሀገር አቀፍና በክልል አቀፍ ደረጃ እየተስተዋሉ ያሉ የፈተና ዉጤት ማሽቆልቆሉም አሰታዉሰዉ ለዚህም ዉጤት ማሽቆልቆል ተብሎ የተለየዉ የፈተናዎች ዝግጅት የጥራት ችግር እንዲሁም ክፍል ዉስጥ የመማር ማስተማር ጉድለት ያለበት መሆኑም አስታዉሰዉ ይህን ችግር ለመፍታት ለመምህራን በአዲሱ ስርዐተ ትምህርት ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።

መምህራኖች አዲሱ ስርአተ ትምህርት በዉስጡ ምን ይዞ መጣ የሚለዉን እንዲገነዘቡ የሚያደርግ እንደሆነም አብራርተዉ እየወሰዱት ያለዉን ስልጠና በተማሪዎች ዉጤትና ስነ ምግባር ላይ የተሻለ ለዉጥ የሚያመጣም እንደሆነም አመላክተዋል።

ክልሉ በመጀመሪያ ዙር 12ኛ ክፍል ማትሪክ በሚሰጥባቸዉ 8 የትምህርት አይነት የያዙ መምህራኖች ቀደም ብሎ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እንደ ዞን 644 መምህራን ፣ርዕሰ መምህራን እንዲሁም ሱፐርቫይዘሮች ማሰልጠናቸዉም ተናግረዋል።

የቸሃ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሀላፊና የወረዳዉ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተማረ ገና እንዳሉት በወረዳዉ 9 ሁለተኛ ደረጃ ትምሀርት ቤቶች የሚገኙ ሲሆን በእነዚህም ከ140 በላይ መምህራን በአንድ ማዕከል ስልጠና እየወሰዱ እንደሆነም ተናግረዋል።

ብልጽግና በጀመረዉ ጉዞ ከአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ጋር እየተሰጠ የለዉ ስልጠና መምህራኖች የሚያነቃቃና በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተጨባጭ ለዉጥ የሚያመጣም እንደሆነም አመላክተዋል።

ስልጠናዉ ለመምህራንና ለርዕሰ መምህራን እንዲሁም ለትምህርት ባለድርሻ አካላት መሰጠቱ በወረዳዉ በ12ኛ ክፍል ፈተና የገጠማቸዉን የዉጤት ስብራት አንደሚቀርፍላቸዉምና በተማሪ ዉጤትና ሰነ ምግባር ላይ የተሻለ ለዉጥ የሚያመጣ እንደሆነም ተናግረዉ

የጉንችሬ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር አቶ አሰፋ ኮሬና በቸሃ ወረዳ የዳቁና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት ወይዘሮ ጤና ለጋ እንዳሉት የአዲሱ ፍኖተ ካርታ የመጽሀፍት ትዉዉቅ ፣ በፈተና ቢጋርና በአጠቃላይ በትምህርት ካሪኩለም በተመለከተ ስልጠና እየተሰጣቸዉ እንደሆነም አብራርተዋል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት እንደ ሀገር አቀፍ የ12 ኛ ክፍል የዉጤት ማሽቆልቆል የገጠመዉና ይህንኑም ለማቃናትና የተማሪዎች ዉጤት ለማሻሻል ይህ ስልጠና አጋዥ እንደሆነም ተናግረዋል።

ካለዉ ንባራዊ ሁኔታ የተነሳ መምህራን እንደዚህ አይነት ስልጠና በየጊዜዉ ለመሰልጠን ምቹ ሁኔታ እንደማያገኙና መምህራን ርዕሰ መምህራኖች በአንድ ላይ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተሰባስበዉ መሰጠቱ የበለጠ በመማር ማስተማሩ ላይ ትልቅ ለዉጥ የሚያመጣም እንደሆነም አብራርተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *