የጉራጌ ዞን ደንና አከባቢ ጥበቃ ልማት ጽ/ቤት ከወረዳና ከከተማ አስተዳደር ጽ/ቤቶች ማኔጅመንት አባላትና ከዞን ባለድረሻ አካላት ጋር በመሆን የጽ/ቤቱ 2014 ዓ.ም የግማሽ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል፡፡
የተሻለ ህይወት ለመኖር ሁሉም ህብረተሰብ አከባቢውን ማልማትና ከብክለት የጸዳ ማድረግ ይገባል፡፡
የምክክር መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የዞኑ ደንና አከባቢ ጥበቃ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት ወንበርጋ እንደተናገሩት የአካባቢ ጥበቃና ልማት ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ የህብረተሰቡን ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተዉ በትኩረት መስራት አለባቸዉ ብለዋል፡፡
የአከባቢ ደህንነት መብቶችን በማስከበር ዜጎችን በንጽህናና በጤናማ አካባቢ እንዲሩ ለማስቻል እንዲሁም ከተሞች ጽዱና አረንጓዴ እንዲሆኑ የደረቅና የፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት ለመዘርጋት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከፋብሪካዎች ወደ አየር የሚለቀቁ በካይ ጋዞች ምክንያት የሚመጣውን ብክለት ለመቀነስ ደኖችን ከጭፍጨፋ በመታደግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለቸውን ደኖችን መትከል አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የዞኑን የደን ሽፋን ወደ 24 በመቶ ማሳደግ መቻሉን በመጠቆም፡፡
አከባቢን የሚበክሉ የደረቅና የፈሳሽ ቆሻሻ አወጋግድ፣ በወንዝ ውስጥ የሚታጠቡ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ ወደ ወንዝ የሚለቀቁ የፋብሪካ ተረፈ ምርቶችን ለመቆጣጠር የዞን፣ የከተማ አመራር ፣ የህግ አካላትና በዘርፉ ያሉ ባለሞያዎች በቅንጅት በመስራት ከተሞችንና አካባቢን ከብክለት የጸዳ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
የ2014 በጀት አመት የግማሽ አመት ዕቅድ አፈጻጸም በጥልቀት ተግምግሞ የሰራ መነቆዋች በመለየት በቀጣይ ተቀናጅቶና ተናቦ መስራት እንደሚገባ አቶ ምህረት ወንበርጋ አሳስበዋል፡፡
የተሻለ ህይወት ለመኖር ሁሉም ህብረተሰብ አከባቢውን ማልማትና ከብክለት የጸዳ ማድረግ ይገባል፡፡
የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና በዘርፉ የሚስተዋሉ የአፈጻጸም ጉድለቶች በፍጥነት ለማረም የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል እንዲሁም የባለሙያ የክህሎት ስልጠና እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
በሴክተሩ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የህግና ሌሎች ተቀዳሚ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ደንና አከባቢ ጥበቃ ልማት ጽ/ቤት፣የወረዳና ከተማ አስተዳድር ጽ/ቤት ማኔጅመንት አካላትና ሙያተኞች፣የውኃና ማእድን፣ንግድና ገበያ ልማት፣ ትምህረት ፣ ኢንቨስትመንት፣ መንገድና ትራንስፖርት ፣እርሻና ተፈጥሮ፣ የዘርፉ ቋሚ ኮሚቴዎችና ማህበራት በምክክር መድረኩ ተሳታፊ ነበሩ ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ፡፡
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx