የአብሮነት የመቻቻልና የመረዳዳት እሴቶቻችን በማጎልበት አንድነታችን ማጠናከር ይኖርብናል ሲሉ በወልቂጤ ከተማ የሚኖሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ገለጹ።

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ’ የመጀመሪያው ጎዳና ላይ ኢፍጣር ፕሮግራም በድምቀት ተካሄደ፡፡

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ረማዳን ሲሆን የእምነቱ ተከታዮች ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት ፈጣሪ ይሰጣቸው ዘንድ ዱዓ በማድረግ ይማጸናሉ።

የረመዳን ወር ማገባደጃ ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ለማስፈጠርና ስለ ሀገራችን ሰላምና አንድነት ዱአ ለማድረግ በወልቂጤ ከተማ የኢፍጣር ፕሮግራም የተዘጋጀ ሲሆን ምስኪኖች የታደሙበት የኢፍጣር ፕሮግራም ነበር።

በፕሮግራሙ የተገኙት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ገብረመስቀል እንደተናገሩት የታላቁ ረመዳንን ወር የአብሮነት፣ የመረዳዳትና የመተዛዘን ወር በመሆኑ ይህ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሀ ግብር መዘጋጀቱ አንዱ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።ለዝግጅቱ መሳካት እገዛ ላደረጉ አካላት በሚሉ ምስጋናቸው አቅርበዋል።

በፕሮግራሙ የታደሙ ህዝበ ሙስሊም በሰጡት አስተያየት የጎዳና ላይ ኢፍጣርን ሲዘጋጅ የረመዳን ወር እዝነት እራህመት ከአላህ የሚገኝበት በመሆኑ ይህ የተጀመረው መልካም ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ዝግጅቱ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ወገኖች የኢድ አጋማሽ በደስታ እንዲያሳልፉ ከማስቻል በተጨማሩ ሁሉም ለሀገራችን ሰላም ፣ አንድነት እና ፍቅር እንዲወርድም ማህበረሰቡ በዱዓ ላይ እንዲበረታ ያደርገዋል ብለዋል።

በከተማው በተከናወነው በዚሁ የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ የዞኑና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ የከተማው ህዝበ ሙስሊምን ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶችም ተሳታፊ ሆነዋል።

በመጨረሻም ለፕሮግራሙ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *