በአብሬት ታሪካዊ መስጅድ የሚገኙ ቅርሶች በተገቢዉ በመጠበቅ ለቱሪስት መስህብት ምቹ በማድረግ ለቀጣይ ትዉልድ ለማስተላፍ በቅርስነት መመዝገብ እንዳለበት ተገልጿል ።
በበዓሉ የተገኙት የአዲስ አበባ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ሀጂ ሙሀጂር ዲኖ እንደገጹት የአብሬት መውሊድ የተለያዩ ብሄረሰቦችን በአንድ ተሰባስበዉ በጋራ ፀሎት የሚያደርጉበት፣የሚረዳዱበት፥የሚተሳሰቡበት እስላማዊ ብሎም ኢትዩጲያዊ እሴት ነው ብለዋል።
በሀድራው የሚገኙ ዕድሜ ጠገብ ቅርሶችን በማልማት አካባቢዉ ለቱሪዝም ሳቢ እንዲሆን በማድረግ ለአካባቢው የገቢ ሚንጭ ሆኖ እንዲያገለግል የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።
በአሉ አከባበር ላይ የተገኙት የቸሃ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙራድ ከድር የዘንድሮ የመውሊድ በዓል የ130 ዓመት ዕድሜ ባለው በታሪካዊ የአብሬት ሀድራ በተለየ መልኩ እንዲከበር የፀጥታ የመንገድ ደህንነትና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራ ከወረዳዉ አመራር ፣ከመስገጂዱ ኮሚቴዎች፣ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ተሰርቶ በድምቀት ሊከበር መቻሉን አብራርተዋል ።
የአብሬት መውሊድ በኢትዮጲያ ውስጥ ከሚከበሩ ትላልቅ ሀይማኖታዊ በአላቶች ተጠቃሽ በመሆኑ ከመላ ሀገሪቱ የሚመጡ በርካታ እንግዶች ለማስተናገድ ወረዳው የበኩሉን እያደረገ ቢሆንም የመንገድ፣ የውሃና ሌሎች የመሠረተ ልማት ችግሮች ለመቅረፍ በየደረጃው የመንግስትና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ይሻል ብለዋል።
በሀድራው ውስጥ ለዘመናት ተጠብቆ የቆዩ የተለያዩ ዕድሜ ጠገብ ቅርሶች መኖራቸው የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው አቶ ሙራድ ይህንን ታሪካዊውን የአብሬት ሀድራና በውስጡ የሚገኙ ቅርሶች ለቱሪስት መስብነት እንዲውሉና በቅርስነት እንዲመዘገብ ለተጀመረው ጥረት በየደረጃው የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፣ ሚዲያዎች፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ ሙህራንና ባለሀብቶች የበኩላቸውን እንወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ሌላው በበዓሉ የተገኙት የቀድሞ የአብሬት ሼህ ደረሳ ኢምራን ሀጅ ኑር ሁሴን በበኩላቸው እንዳሁን ቴክኖሎጂ እንኳ በሌለበት ወቅት ምዕመኑ ማንም ሳይጠራው ወቅቱን አውቆ ከአራቱ የሀገሪቱ ማዕዘናት በመሰባሰብ የተቸገረ የሚረዳበት ለሀገር ሰላምና አንድነት ዱዓ የሚደረግበት በዓል እንደሆነ ተናግዋል።
የአብሬት መስጂድ በርካታ መፅሀፍት በነበዩ መሀመድ( ሠዐወ)፣ በባልደረቦቻውና በትላልቅ የሀበሻ መሻኢሆች የሚያጠነጥኑ በርካታ የታተሙና ያልታተሙ መፅሀፍትን በመፃፍ ለመዕመኑ አበርክተዋል ብለዋል።
አክለውም ህብረተሠቡም በዓሉን ሼሆች ባስቀመጡት ጥሩ ስነ ምግባር መሠረት እሴቱን ለትውልድ እንዲተላፍ መሠራት አለበት ብለዋል ።
አስተያየታቸው ከሰጡን የበአሉ ታዳሚዎች መካከል አቶ ደጉ በቀና፣አቶ ፈድሉ አረቦና ጀማል ኸሊፍ በዓሉ እርስ በርስ የሚገናኝበት ፣ አብሮ የመብላትና የመረዳዳት ባህል የሚጎለብትበት፣ አቅም ለሌላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚረዱበትና ለሀገር ሰለምና እድገት በጋራ ዱአ ወይም ፀሎት በማድረግ የሚያከብሩት በዓል እንደሆነ ተናግረዋል።
በአብሬት ታሪካዊ መስጅድ የሚገኙ ቅርሶች በተገቢዉ በመጠበቅ ለቱሪዝም ምቹ በማድረግ ለቀጣይ ትዉልድ ጠብቆ ማቆየት እንዲቻል የበኩላቸውን እንደሚወጡ የገለፁት አሰተያየት ሰጪዎቹ ቀጥሎ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም የበዓሉ ተሳታፊዎች ተናገረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx