የአርሶ አደር ትርፋማነትን የሚያጎላ የግብርና ስራ ውጤታማነት እንዲጭምር የመስቃን ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ከ ( snv-Hort life project ) ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል።

ኤስ ኤን ቪ ሆርቲ ላይፍ ፕሮጀክት ከመስቃን ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት በሆርቲካልቸር ስ/ሂደት በወረዳችን በስፋት ከሚመረቱ የአተክልት ሰብሎች ውስጥ በ4 ዓይነት የአተክልት ሰብሎች አነስተኛ ገቢ ካላቸውን አ/አደሮች በጋራ በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ።

የመስቃን ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ምርታማነትን ከሚችሩ ዘርፈ ብዙ የግብርና እንቅስቃሴዎች መካከል ከእንደዚህ አይነት የልማት ፕሮጀክቶች ጋር የገበሬውን ልምድና ውጤታማነት ለማጎልበት ትስስር በመፋጠር የአርሶ አደሩን የግብርና ክህሎት በዘመናዊ መንገድ ማዳበር እና ተጠቃሚ ማድረግ ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

በዚህም መሰረት በsnv-Hort life project ከግብርና ልማት ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን በአይነቱ ለየት ያለ ስያሜውም ” ተቋማዊ ማድረግ” ወይም ” Institutionalized practice” የሚል ሲሆን በተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚተገበሩ ውጤታማነታቸውን በአርሶ አደራችን የተረጋገጡ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ፕሮጀክቶቹ የሰራ ጊዜያቸው ቢያበቃም ተግባሩን ግን የመንግስት ተቋማት ባገኙትና ባዳበሩት የስራ ልምድ በመነሳት ምርጥ ተግባራቶችን በማስቀጠል ”ተቋማዊ/institutionalized ማድረግ ይኖርባቸዋል በሚል – ከተሻሻሉና ከዘመናዊ የአተክልት አመራረት በተጨማሪ የአ/አደሩን የአመጋገብ ስርዓት እንዲሻሻል ያደርጋል።

ምርታመነታቸው ከፍተኛ የሆኑ፣በሽታን ሊቋቋሙና በገበያ ተፈላጊ የሆኑ የአተክልት ሰብሎችን ያስተዋውቃል፣- በገበያ በጥራት ይዘታቸው የተረጋገጡና ተፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በማምረት የአ/አደሩን ገቢ ከፍ እንዲል ማድረግ- በወረዳችን በ5 የውሀ አማራጭ ባላቸው ቀበሌዎች በመለየት- በተለዩ ቀበሌዎች በእያንዳንዱ ቀበሌ 2 የአርሶ አደር የመስክ ት/ቤት ያቋቁማል።

በአንድ የአርሶ አደር የመሥክ ት/ቤት 4 መሪ አ/አደሮችንና ከ30 ያላነሱ ሌሎች ተከታዮችን በማካተት በየ15 ቀኑ ቴክኖሎጂዎችን በተግባር ይከታተላሉ።

ባሁኑ ወቅት በጠቅላላው 40 መሪ አርሶ አደሮችን በ5 ቀበሌ በአራት የአተክልት ሰብሎች በመልማት ላይ ይገኛል በቲማቲም፣በቃሪያ፣በቀይ ሽንኩርትና በጥቅል ጎመን ሰብሎች የተሻሻሉና ዘመናዊ የሆኑ የአመራረት ዘዴዎችን በተግባር በአ/አደሩ ማሳ የአ/ አደር የመሥክት ላይ ት/ቤት(farmer field school) ይመሠርታል፣እስከ መጨረሻው ምርት ድርስ ይደግፋል-በአ/አደሩ ማሳ ላይ ለሚሰሩ ሰርቶ ማሳያዎች የዘር፣የማዳበሪያና የኬሚካል ወጪን ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል።

በቀበሌ፣በወረዳ፣በዞን እና በክልል ደረጃ በተሰሩ ሰርቶ ማሳያዎች ላይ የተሰሩ የምርጥ ተሞክሮ የስርፀት ደረጃን በመለየት ለቀጣይ ዙር ቀምሮ ለሌሎች አ/አደሮች ያስተላልፋል።

በየ 15 ቀኑ መሪና ተከታይ አርሶ አደሮች በተሻሻሉ የአተክልት ሰብሎች አመራራት በተጨማሪ በስርዓተ ፆታ ላይ ለአ/አደሮች የማነቃቂያ አጫጭር ስልጠናዎችን ይሰጣል።

በመጨረሻም የወረዳው ግብርና አርሶ አደሩን የሚጠቅም ዘርፈ ብዙ የምርታማነት አማራጮችን በመጠቀም የለውጡ አካል ማድረግ ይገባል በዚህም የብዙዎች የማይተካ ሚና እንደሚያሻ ገልጸዋል ሲል የመስቃን ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቦታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *