የአርሶ አደሩ የግንዛቤ ለውጥ በመፈጠሩ በሁሉም ቀበሌዎች በቆሎን በክላስተር ማልማት መቻሉን ተገለፀ።


በበልግ ከታቀደው 40 ሺህ ሄክታር ውስጥ 33 ሺህ 5 መቶ 60 ሄክታር በዘር በመሸፈን ወረዳው የበቆሎ ቤልት ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።

በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሱ ጁሃር በግብርናው ዘርፍ በ2016 በበልግ ከታቀደው 40 ሺህ ሄክታር ውስጥ 33 ሺህ 5 መቶ 60 ሄክታር በክላስተር ማልማት መቻሉን ገልፀዋል።

በተለይ የበቆሎ ክላስተር በሚል በተወሰኑ ቀበሌዎች ብቻ ይለማ የነበረው አሁን የአርሶ አደሩን ግንዛቤ በመለወጥና በማስፋት በሁሉም ቀበሌዎች በቆሎን በክላስተር በማልማት ወረዳው የበቆሎ ቤልት ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል።

እነደ ሀገር እራስን በምግብ የመቻል እስትራቴጂክ ይፋ ከተደረገ በኃላ የወረዳው አመራር ፣ አርሶ አደሩና ባለሙያው በቅንጅት በመስራት ምርትና ምርታማነት እያደገ መምጣቱን ገልፀዋል።

በመኸር 29 ሺህ 53 ሄክታር ለማልማት ታቅዶ 8 ሺህ 2 መቶ 47 ሄክታር የለማበት ሂደት መኖሩን ገልፀው በዘርፉ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ግብአትና ምርጥ ዘር ድርሻቸው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።

የግብአትና የምርጥ ዘር አቅርቦት ከሌላው ጊዜ የተሻለ ቢሆንም ከወረዳው ሰፊ የማልማት ፍላጎት አንፃር አሁንም ጉለት መኖሩን ገልፀዋል።

ተግባራዊ እየተደረገ ያለው 30፣ 40 እና 30 የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት ጥሩ በሚባል መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ጨምረው ገልፀዋል።

የአበሽጌ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ተወካይና የእርሻ ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሙላቱ ደሳለኝ በበኩላቸው በቆሎን በክላስተር 35 ሺህ ሄክታር ለማልማት ታቅዶ 33 ሺህ 5 መቶ 60 ሄክታር በዘር መሸፈኑን ገልፀዋል።

ክላስተሪንግ አፕሮች በአ/አደሩ መካከል ፉክክር እንዲኖርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በመንግሥት የወረደ ኢንሼቲቭ ነው ያሉ ሲሆን እንደ ወረዳ ይህን ደረጃ አልፈን ወደ ሜጋ ክላስተሪንግ መገባቱን ገልፀዋል።

የተፈጥሮ ሃብትን በዘላቂነት በማልማትና በመጠበቅ ምረትና ምርታማነትን ለማሳደግ ጠቃሚነቱ በተግባር የተረጋገጠው የአረንጓዴ አሻራ ተግባር በስፋት እየተከናወነ መሆኑንም አቶ ሙላቱ ጨምረውም ገልፀዋል።መረጃው የአበሽጌ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *