የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በግብርናው ዘርፍ የሚፈለጉ ግብአቶችን ለማሟላት በትኩረት አንደሚሰራ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

መስከረም 14/2015

የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በግብርናው ዘርፍ የሚፈለጉ ግብአቶችን ለማሟላት በትኩረት አንደሚሰራ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

ኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ ተጠቅመን በመስራታችን በግብርናው ዘርፍ የበለጠ ውጤታማ እንድንሆን አድርጎናል ሲሉ የሶዶ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።

ይህን ያሉት በትናንት ዕለት የተለያዩዩ ሚስተሮች በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ በመኸር በተለያዪ ሰብሎች የለሙ ማሳዎችን በጎበኙበት ወቅት ነው።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በጉብኝቱ ተገኝተው ባስተላለፊት መልዕክት በየጊዜው አርሶ አደሩ በክላስተር በማልማቱ በዞኑ የግብርና ስራ ላይ ውጤት ታይቷል።

የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በግብርናው ዘርፍ የሚፈለጉ ግብአቶችን ለማሟላት በትኩረት አንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በተለይም የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ ባለፉት ሁለት አመታት ከባንክ ብድር በመውሰድ የትራክተር ግዢ በመፈጸም ለአርሶ አደሩ መከፋፈሉ አስገንዘበዋል።

እንደ መሀመድ ገለጻ በሀገራችን በተፈጠረው ጦርነት የሚከሰተው የምግብ እጥረት ለመቀነስ አርሶ አደሩ የግብርና ስራው በማጠናከርና ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ በማድረግ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሆነ ገልጸዋል።

የዞኑ አርሶ አደሮች፣ሴቶችና ወጣቶች ተደራጅተው በክላስተር በመስራት ከራሳቸው አልፈው ሀገራችን ከውጭ ጠባቂነት እንድትላቀቅ እየሰሩ እንደሆነ አቶ መሀመድ አስታውቋል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በዘንድሮ በመኽር ወቅት 148 ሺህ 121 መሬት ለማልማት ታቅዶ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆኑ አስታውቋል።

በዘንድሮ መኽር ወቅት በጤፍ በገብስ በሌሎች በጥራጥሬ ሰብሎች በስፋት ማልማት የተቻለ ሲሆን በተለይም በስንዴ በ8 ወረዳዎች በ125 ቀበሌ 1067 ክላስተር 23 ሺህ 750 በኩታ ገጠም እየለማ ነው ብለዋል።

በመኽር ወቅቱ የኩታገጠም ስራ ትኩረት የተሰጠው ተግባር እንደነበር ያስተወሱት ኃላፊው ይህ ደግሞ አርሶ አደሩ በአንድነትና በመተጋገዝ እንዲሰራ አስችሎታል ሲሉ ተናግረዋል።

የሶዶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሴ አበጋዝ በንግግራቸው በወረዳው በመኸር ሰብል 35 ሺህ ሄክታር መሬት የለማ ሲሆን ከ1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል ብለዋል።

በዚህ በመኸር ወቅት በክላስተር ይለማል ተብሎ ከታቀደው ማሳ ውስጥ 13 ሺህ 334 ሲሆን በዚህም 7ሺህ 7መቶ አርሶ አደሮችን ተሳትፈዋል ነው ያሉት።

በወረዳው ያገኘናቸው አርሶ አደሮች እንዳሉት ኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ ተጠቅመን በመስራታችን በግብርናው ስራ ውጤታማ እየሆንን ነው ብለዋል።

ይህ ቢሆንም በግብርናው ዘርፍ የበለጠ ውጤታማ እንዳንሆን የመሰረተ ልማት፣የማዳበርያና የትራክተር ችግሮች ማነቆ ስለሆነብን በቀጣይ ጊዜያት ሊቀረፉልን ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
መልካም መስቀል በጉራጌ !!

ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *