የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማረጋገጥ የግብርናው ዘርፍ ማዘመን እንደሚገባ የእኖር ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ።

ነሐሴ 16/2014

የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማረጋገጥ የግብርናው ዘርፍ ማዘመን እንደሚገባ የእኖር ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ።

በወረዳው በመኸር ከሚለማው እርሻ 1መቶ 10ሺ 8መቶ ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ ተጥሎ እየተሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

በእኖር ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብድልመጂድ ጀማል በወረዳው የመኸር እርሻ ውጤታማ እንዲሆንና የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዘንድሮ መኸር እርሻ በወረዳው 5ሺ 688 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 5ሺ 6መቶ 67 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈን ተችላል ብለዋል።

በዚህም 1መቶ 10ሺ 8መቶ ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ ተጥሎ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት።

የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተለያዩ የመካናይዜሽን ስራዎች መሰራታቸው የተናገሩት ኃላፊው የአርሶ አደሩ ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ቆጣቢ በሆነ መልኩ በትራክተር እንዲያርሱ መደረጉንም ገልጸዋል።

በመኸር ከሚለማው አጠቃላይ ማሳ ጤፍ 2ሺ 3መቶ 96 ሄክታር፣ ስንዴ 3መቶ63 ሄክታርና ገብስ 5መቶ 30 ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም መልማቱን ተናግረዋል።

ከግብአት ጋር ተያይዞ 3ሺ 5መቶ 66 ኩንታል Nps እና 1ሺ1መቶ 10 ኩንታል ዩሪያ እና 1መቶ50 ኩንታል የስንዴና 60 ኩንታል የጤፍ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ ማስራጨት ተችሏልም ብለዋል። በዚህም የዩሪያ እጥረት እንደነበርም በመጠቆም።

የግብርናው ዘርፍ በማዘመን የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ የገለጹት አቶ አብድልመጂድ የአርሶ አደሩ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ የግብአት አቅርቦትና ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን መንግስት አቅዶ ሊሰራባቸው ይገባል ብለዋል።

ወጣት ረጂብ ሙደሲርና ወጣት በድሩ አባሜራ በእኖር ወረዳ በጡማነ ቀበሌ በማህበር ተደራጅተው በበልግና በመኸር እርሻ ሲያለሙ ያገኘናቸው ወጣቶች ናቸው።

እንደ ወጣቶቹ ገለጻ ከዚህ በፊት በበልግ ወቅት ድንች በማልማት ውጤታማ መሆናቸውን አስታውሰው በመኸር እርሻ ወቅትም ከባለሙያ ያገኙትን ምክረ ሃሳብ በአግባቡ ተጠቅመው እያለሙ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ተደራጅቶ መስራት በአንድነት መንፈስ ስራዎችን በመተጋገዝ ለመስራት ያግዛል ያሉት ወጣቶቹ ቁጥቋጦ መንጥረውና ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ማሳቸው ማረሳቸውን ጠቁመው በአሁኑ ወቅት የአረም ቁጥጥጥር ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውም ተናግረዋል።

አክለውም ምርትና ምርታማነታቸውን በማሳደግ የምግብ ፍጆታቸውን ከመቻል ባለፈ የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልፀው ለዚህም መንግስት ከግብአት ጀምሮ አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግላቸውም ጠቁመዋል።

መረጃዎቻችበተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *