የትምህርት ስርአቱ ውጤታማና ችግር ፈቺ እንዲሆን በሳይንስ፣በፈጠራና በሂሳብ ትምህርቶች ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።

የእዣ ወረዳ የትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት “ፈጣሪና ተመራማሪ ዜጋ መፍጠር” በሚል መሪ ቃል የሳይንስ፣የፈጠራና የሂሳብ ስራዎች ውድድር እና ኤግዚቢሽን በአገና ከተማ ዛሬ ተካሂዷል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ በዚህ ወቅት እንዳሉት የትምህርት ስርአቱ ውጤታማና ችግር ፈቺ እንዲሆን የሳይንስ፣የፈጠራና የሂሳብ ስራዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራበት ገለጸዋል።

በአሁን ወቅት መንግስት ለትምህርት ጥራት የተለየ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራበት መሆኑ ገልፀው ለዚህ ደግሞ ተማሪዎች ያገኙት እውቀት ወደ ውጤት ቀይረው ማህበረሰቡ በሚጠቅም መልኩ ብሎም የሳይንስና በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ መሰራት አለበት ነው ያሉት።

ያለ ትምህርት ስልጣኔ የለም ያሉት አቶ ክብሩ ሀገራችን እንድታድግ የትምህርት ስራ በቴክኖሎጂና በፈጠራ ስራዎች ማገዝ እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የእዣ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤቶች ኃላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ እንደገለፁት ተማሪዎች የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ዝንባሌያቸው አነሳ እየሆነ በመምጣቱ ቀጣይ ፍላጎታቸው እንዲጨምር የፈጠራ ስራዎች ውድድርና ኤግዚቢሽን መዘጋጀቱ መሰረታዊ መፍትሄ ይሆናል።

ዘርፉን ለማጠናከር በግብአት፣ በበጀትና በቁሳቁስ ለመድገፍ ከወረዳው አስተዳደር፣ ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራበት ገለጸዋል።

በየክላስተሩ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን ተካሂዷል ያሉት ኃላፊው እንደጥቅል ደግሞ በአንድ ማእከል ከ15 እስከ 20 የተመረጡ የፈጠራ ስራዎች ለውድድርና ለእይታ መቅረባቸው አሳውቀዋል።

ተማሪዎቹ ከወዳደቁ ቁሰመቁሶች በአካባቢው የሌሉና ከውጭ ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁ ቁሳቁሶች ለይተየው መስራታቸው አሳውቀዉ ለአብነትም በሆስፒታሎች የህጻናት ማሙቂያ፣ኬላ መገደቢያ ማሽን፣እስቴዲየም፣የመንገድ ላይ ትራፊክ፣ሪል እስቴት፣የመከላከያ ሰራዊት የመገናኛ ሬድዮ ከአልባሳቱ ጋር በማድረግ ቻርጅ የሚደረግበት ማሽንና ሌሎችም ሰርተው በኤግዚቢሽኑ አቅርበዋል ብለዋል።

ቀጣይ ተመራማሪ ዜጋ ለማፍራትና ሀገር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀመረችው ጥረት ለማሳድግ ተማሪዎች የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ላይ እንዲያዘወትሩ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፏል።

ተማሪ ጸሀይ አገዢ፣ዳንኤል መንግስቱ፣አማኑኤል ኑርሰፉና ይስሀቅ ብላቱ በእለቱ የፈጠራ ስራቸው ያቀረቡ ተማሪዎች ሲሆኑ ለአካባቢው ማህበረሰብ ችግር የሆኑ ጉዳዮች መፍትሄ ለመስጠት የፈጠራ ስራዎች እንድንሰራ ተነሳስተናል ብለዋል።

በተለይም ሀገራችን ሁሌም ድሀ ናት በሚል እሳቤ አብዛኛው መሳሪያዎች ከውጭ እየገቡ በመሆኑና ሀገሪቱ ማግኘት ያለባት ጥቅም እያገኘች ባለመሆኑ ቁጭት ይፈጥራል ያሉት ተማሪዎቹ ይህንን ለማስቀረት የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

ቀጣይም ተገቢው ድጋፍና ክትትል ከተደረገላቸው የማህበረሰቡ ችግር የሚፈቱና ሀገርን በቴክኖሎጂ እንድትበለጽግ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ ጨምሮ የወረዳው አመራሮች፣መምህራን፣ተማሪዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ትምህርት ቤቶች የእውቅናና የሽልማት ስነስርአት በማካሄድ ተጠናቋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *