የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የማህበረሰቡ ችግር ፈቺ የሆኑ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች በመፍጠርና በመቅዳት እያደረጉት ጥረት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ አስታወቀ።

ለ4 ተከታታይ ቀናት በወልቂጤ ከተማ ሲካሄድ የነበረው ባዛርና ኢግዚቢሽን በዛሬ እለት ተጠናቀቀ።

የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈቱ አብዶ እንደገለጹት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በባዛርና ኤግዚቢሽን ለማህበረሰቡ ችግር የሚፈቱ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳትና በመስራት አቅርበዋል።

ለዘርፉ ውጤታማነት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና ኢንተረፕራይዞች በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

በወልቂጤ ከተማ ተዘጋጅቶ በነበረው ባዛርና ኢግዚቢሽን በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች 18 የተለያዩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ ማቅረብ እንደተቻለም አስታዉቀዋል።
ከነዚህም 7ቱ የተሸጋገሩና ሀብት የፈጠሩ 11ደግሞ በአሁን ወቅት እየተሸጋገሩ ያሉ ናቸው ብለዋል ።

በዞኑ ካሉ 12 ቴክኒክና ሙያዎች ኮሌጆች የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም የፈጠራ ስራቸው ያስተዋወቁና ለገበያ ያቀረቡ ሲሆን ለአብነትም የበቆሎ መፍጫ፣ የእንሰት መፋቂያ፣የከብቶች መኖ ማቀነባበሪያ፣ አምቾ መከትከቻ፣ቡላ ማድረቂያና የጤፍ መውቂያና ሌሎችም ቴክኖሎጂዎች በባዛርና ኤግዚቢሽን ማቅረብ እንደተቻለም አብራርተዋል።

ኮሌጆች ስራ ፈጣሪ ሰልጣኞችን በማፍራት፣ የተለያዩ የህብረተሰቡ ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ የፈጠራ ስራዎች በማዘጋጀት፣አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለኢንተርፕራየዞች በማሸጋገር እንዲሁም ሙያዊ ድጋፍና ክትትል በማድረግና ስልጠናዎች በመስጠት በርካታ ተግባራት የሚያከናውኑ ሲሆን ይህን ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል አካዳሚክ ዲን አቶ አጅመል መሀመድ በበኩላቸዉ በወልቂጤ ከተማ ተዘጋጅቶ በነበረው ባዛርና ኢግዚቢሽን ላይ በየ ዲፓርትመንቱ የማህበረሰቡ ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ ስራዎች መቅረባቸው ገለጸዋል።

በኢግዚብሽኑ ለናሙና የቀረቡ ቴክኖሎጂዎች በማህበረሰቡ በመተቸታቸው ለቀጣይ የበለጠ መስራት እንደሚያስፈልግ ግብአት ተሰብስቧል ነው ያሉት።

በማኒፋክቸሪንግ ፣በጨርቃጨርቅ፣በኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ሳምፕል የቀረቡ ሲሆኑ ሌሎቹ ለማህበራት እንዲሸጋገሩ መደረጋቸው ገልጸዋል።

በሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ተሰርቷል ያሉት አቶ አጅመል ከነዚህም ለህብረተሰቡ ፍላጎት ባማዘኑት በተለይ የግብርና እና ከእንሰት ቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ እንደሆኑ ጠቅሰዋል።

ባዛርና ኢግዚብሽኖች መዘጋጀታቸው ተማሪዎች በግቢው ውስጥ እየሰሩት ያለው ስራ ምን እንደሆነ ለህብረተሰቡ ለማሳወቅና ግንዛቤ እንዲኖረው ያስቻለ ነው ብለዋል አቶ አጅመል።

አያይዘውም በግል የሚሰሩ ወጣቶች የተለያዩ ስራዎቻቸው ለኢግዚብሽን ማቅረባቸው አስታዉቀዉ በቅርቡ 72 ተማሪዎች ደግሞ ቡታጅራ ደስታ ጋርመንት ፋብሪካ እንዲቀላቀሉ መደረጉም ጠቁመዋል።

በየጊዜው ባዛርና ኢግዚቢሽኖች መዘጋጀታቸው ኮሌጆች የሚሰሩት ስራ ለህብረተሰቡ የማሳወቂያ መንገድ ከመሆኑም በተጨማሪ የህብረተሰቡ ግንዛቤ እየጨመረ መጥቷል ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *