የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የገበያ ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ብቁና ተወዳዳሪና የሠለጠነ የሠው ኃይል በማፍራት ሀገራችን ለሚታደርገው የብልጽግና ጉዞ ድርሻዉን እንዲያበረክት ዘርፉ የአመራር ትኩረት እንደሚያስፈልገዉ የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያዉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ላይ እና በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ወቅት ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ከኮሌጆች ዲንና ከቦርድ አመራሮች ጋራ ውይይት በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል ።

የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈቱ አብዶ እንደገለጹት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በራሱ የሚተማመን ብቁ የሰለጠነ የሠው ኃይል በማፍራት፣ ለሀገር ውስጥ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ለመንግስት ተቋማት እንዲሁም ወደ ውጭ ሀገር በመላክ ወጣቱ ለራሱና ለሀገር የሚጠቅም የኢኮኖሚ አቅም እንዲፈጥሩ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በመደበኛ፣ በአጫጭር ስልጠና፣ በማታ እና ቅዳሜና እሁድ የሰልጣኞች ቁጥር ማነስ እና ዕድሉን ባግባቡ አለመጠቀም መሠል በኮሌጆች የሚስተዋሉ ችግሮችን የቦርድ አመራሩ በባለቤትነት ድጋፍና ክትትል በማድረግ እንዲሁም ከሌሎች በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ተቀናጅቶ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

አቶ ፈቱ አብዶ ይህን ያሉት በዞኑ ከሚገኙ ኮሌጆች የተከፈቱ የስልጠና ክፍሎች በሠልጣኝ እጥረት መዘጋቱ ጠቃሚ እና በውድ ዋጋ የተገዙ ማሽነሪዎች የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እየሠጡ እንዳልሆነ አስታዉሰዉ በአጠቃላይ ተቋማቱ ካላቸው የሰው ኃይልና ግብዓት አቅም ልክ የሠለጠነ የሠው ኃይል ማፍራት ያልቻሉ ኮሌጆች ያጋጠማቸው የአመለካከት ችግር ለመፍታት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በጥራትና ተፈላጊ በመሆን ዘላቂ ለውጥ በማምጣት ሀብት እንዲያፈሩ እና በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በሚያስችል መልኩ የመደገፍ ስራ ይሰራል ብለዋል።

ለዚህም በየደረጃው የሚመለከታቸው የተለያዩ መስሪያ ቤቶች በተሻለ መልኩ በቅንጅት በመስራት ሞዴልና በሥራቸው ውጤትማ የሆኑ ኢንተርኘራይዞች ማፍራት ላይ ትኩረት ተሠጥቶ ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ኮሌጆች ለአርሶአደ ደሩ፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን እንዲሁም ሌሎች የመንግስት ተቋማት የአሰራር ስርዓቱ ተረድቶ ችግር ፈቺ የሆነ ቴክኖሎጂ ለማፍለቅና ለማላመድ ርብርብ ማድረግ ይጠቅመዋል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የቦርድ አመራሮች ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በመማር ማስተማር ሂዲት የሚገጥማቸውን የአመለካከትና የግብዓት ችግሮችን ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ተቀራርቦ በመነጋገር ዘርፉን ውጤታማ ማድረግ ይገባል ።

በዞናችን ከሚገኙ ኮሌጆች መካከል የወልቂጤና የቡታጅራ እንዲሁም ሌሎች በግብዓትና በሠለጠ የሠው ኃይል የተሻለ አቅም ካላቸው ጋር ልምድ ልውውጥ የማድረግና እርስበርስ የመደጋገፍ ባህል የበለጠ ማዳበር እንደሚገባ ገልፀዋል ።

ወጣቱ ትውልድ በምርታማነትና ጥራት በሚያሻሻሉ የክህሎት ስልጠና በማግኘት ሀገር በቀል እና ከውጪ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን በማሻሻል በመቅዳት እና በማባዛት በግሉ ከሚያገኘው ጠቀሜታ ባሻገር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ በአግባቡ ለማስገንዘብ የአመራር ትኩረት ይጠይቃል ብለዋል።

ለዚህም የኮሌጅ ቦርድ አመራር ከወረዳና ከተማ መስተዳድሮች ካሉ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጀቶ በመስራት በዘርፉ የተጣሉ ግብ እንዲያሳኩ የድርሻውን እንዲወጡ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ኃላፊው አቶ አበራ አለሙ በ2014 ዓ.ም የሀገር አቀፍ የ12ኛ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ገብተው መሠልጠን የሚገባቸውን ተማሪዎችን በወቅቱ ተመዝግበው ተገቢውን ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ፖሊስ እና ስትራቴጂ ውስጥ
ሀገር በቀል እውቀቶችን የሚያሳድግ እና የአካባቢ ጸጋን የሚያጎለብቱ፣ የሴቶችን ጫና የሚቀንሱ እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ቴክኖሎጂዎችን ለይ ትኩረት መደረጉ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል ።

በድህነት ለመውጣት ሀገራችን ከግብርና መር ወደ ኢንደስትሪ መር ለምታደርገው ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ወሳኝ ተቋም በመሆኑ አሁን የሚስተዋሉ የአመለካከት ችግር ለመቅረፍ ከመደኛ ትምህርት ከሌሎች በለድርሻ አካላት ተቀናጅተን እንሠራለን ብለዋል።

ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን የሚተኩ ቴክኖሎጂዎችን ለማፍለቅ እና ለመቅዳት እንዲሁም ሰርቶም ለማሸጋገር በቀረበው የቴክኖሎጂ ሃሳብ ላይ ቀጥተኛ የሚመለከታቸውን የኢነተርፕራይዝ እና የኢንዱስትሪ ባለሞያዎች፤ የማህበረሰብ አካላት ከንድፈ ሃሳብ ጀምሮ አሳታፊ በሆነ መልኩ እንሚሠሩ አሰተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል ።

የስልጠና መድረኩ ወቅታዊና ጊዜውን የጠበቀ መሆኑን ገልፀው ለተግባራዊነቱ የድርሻቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *