የቱሪዝም ሀብቶች ማልማት ፣መንከባከብና ተጠብቀዉ እንዲቆዩ ማድረግ ይገባል።

ነሀሴ 11/2014

የዓርባን ዋሻ

የቱሪዝም ሀብቶች ማልማት ፣መንከባከብና ተጠብቀዉ እንዲቆዩ ማድረግ ይገባል።

በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከሚገኙ ተፈጥሯዊ ከሆነ የቱሪስት መስህቦች ውስጥ የዓርባን ዋሻ አንዱ ነው።

እድሜ ጠገብ ደኖች፣ ዋሻዎች፣የሀይማኖት ተቋማት፣ ፍልውሃና ፏፏቴዎች በወረዳችን የሚገኙ የቱሪስት መስህቦች ሲሆን ለዛሬ በወረዳው ጎምራ ቀበሌ የሚገኘውን ተፍጥሯዊ ዓርባን ዋሻ የምናስቃኛቹ ይሆናል።

የአርባን ዋሻ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በጎምራ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የሚገኝ ተፈጥሯዊ ዋሻ ሲሆን ከመዲናችን አዲስ አበባ በ145 ኪ.ሜ ሲገኝ ከወረዳችን ዋና ከተማ ከመሃል አምባ በ22 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል።

አርባን ዋሻ ተፈጥሯዊ ሲሆን በወንዝ ዳርቻ የሚገኝና የዋሸው ሰው መግቢያ በር 5 ሜትር ርዝመት ያለውና የውስጥ ክፍሉ ከመሬት 2·2 ሜትር ከፍታ ሲኖረው የውስጥ ለውስጥ ርዝመቱ ከ85 ሜትር በላይ ሲረዝም የጎኑ ስፋት ደግሞ ከ20—30 ሜትር ስፋት ያለው ማረኪ ዋሻ በመሆኑም ከዞናችን በቁመቱም በስፋቱም እንዲሁም በርዝመቱም ቀዳሚ ከሆኑ ዋሻዎች አንዱ ነው።

በዋሻው ዙሪያ የተለያዩ የዱር እንሰሳትና አዕዋፈት ተሽቆጥቁጦ ልዩ ውበትን የተጎናፀፈ ነው ።

ይህ ዋሻ ለተለያዩ የምርምር ስራዎች በተለይም ለአርኪዮሎጂ አጥኚዎች ምቹ ሲሆን የአርኪዮሎጂ ባለሙያዎች ቢያጠኑት ተጨማሪ ግኝቶች ማግኘት እንድሚችሉ መገመት ይችላል።

በተጨማሪም ስፍራው ለቱሪስቶች ምቹና ሳቢ የቱሪዝም መዳረሻ በመሆኑ ሁሉም ወደዚህ ድንቅ ተፍጥሯዊ ስፍራ በመምጣት መንፈስዎንና አእምሮዎትን አድሰው ይመለሳሉ ሲል የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን ዘግቦታል።
ይምጡና ይጎብኙ ይዝናኑ!!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *