የተጀማመሩ የስራተ ምግብ ስራዎች ከሌማት ትሩፋት ተግባራት አቀናጅቶ በመስራት ጤናው የተጠበቀ ህብረተሰብ መፍጠር እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

መጋቢት

በጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አዘጋጅነት በቸሀ ወረዳ በስራአተ ምግብ የተሰሩ የልማት ስራዎች የመስክ ምልከታ ተደርጓል።

የምስክ ምልከታውም በወረዳው በስራአተ ምግብ የተሰሩ አመርቂ ስራዎች በሌሎች ወረዳዎችም አስፍቶ ለመስራት አላማ ያደረገ ነው።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለጻ የእናቶችና ህጻናት ሞት ለመቀነስና ንቁ ትውልድን ለመፍጠር የስረአት ምግብ ስራ ከሌማት ትሩፋት ጋር በማስተሳሰር በሁሉም አካባቢዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ ከተለምዶ የአመጋገብ ስራት በማውጣት የተመጣጠነ ምግብ እንዲመገብና ድርቅን መቋቋም የሚችሉ ምርቶችን እንዲመረቱ መክረዋል።

በጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አቶ ሰለሞን ጉግሳ በበኩላቸው የስርአተ ምግብ ተግባር በማህበረሰቡ ጤናና ኢኮኖሚ የሚያስከትለው ጫና ከፍተኛ ነው።

በአንድ አንድ መዋቅሮች ለዘርፉ የሚሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑን ያስታወቁት አቶ ሰለሞን ያሉንን ሀብቶች ወደ ስራተ ምግብ ተግባር በማቀራረብ በእናቶችና በህጻናትና ላይ የሚታየው ሞትና መቀንጨር ለመቀነስ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።

ዘርፉ የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ አስፈላጊውን በጀት መመደብ፣የተመደበውም በጀት ለታለመለት አላማ በማዋልና የህብረተሰቡ ግንዛቤ ማሳደግ እንደሚገባ ኃላፊው አስታውቋል።

ጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ የእናቶችና ህጻናት ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ቸሩ አሰፋ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት በአመቱ ለእናቶችና ህጻናት የአንጀት ጥገኛ ትላትል ክትባት፣ የግብርና ግብአቶች እና ሌሎችንም አስፈላጊውን ድጋፍ ሲደረግ መቆየቱን አብራርተዋል።

የቸሀ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ከፋ ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ በትምህርት ቤቶች ክበባትና የቀበሌ የስራተ ምግብ ኮሚቴ ከማቋቋም ጀምሮ እንዲሁም ድጋፎችን የማጠናከር ስራ በመሰራቱ የማህበረሰቡ የአመጋገብ ስርአት ላይ መሻሻሎች እየታዩ እንደሚገኝ ተናግሯል።

በቸሀ ወረዳ የስራተ ምግብ ስራ ተግባራዊ አድርገው የሚጠቀሙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉት በሚሰጣቸው ግብአቶች ቤታቸው ወስደው በመተግበራቸው በተለይ ነፍሰ ጡር እናቶችና ህጻናቶች የተመጣጠነ ምግብ እየተመገቡ እንደሆነ አስታውቀዋል።

በታዩ የመስክ ምልከታ ስራዎች ለወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩ፣ህብረተሰቡ የአመጋገብ ባህሉን እንዲቀየር የሚሰሩ ስራዎች እንዲጠናከሩና ተራዶ ድርጅቶችም የበለጠ እንዲደግፉ ሀሳብ ተሰጥቷል።

በመድረኩም የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣የመምሪያው ኃላፊና የማኔጅመንት አካላት፣ የዞን አመራሮች፣የወረዳና የከተማ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ዘርፉ የሚደግፉ ተራዶ ድርጅቶች፣ የስርአተ ምግብ የቴክኒክና የአብይ ኮሚቴዎች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *