የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራ ትኩረት አድርገዉ በመስራታቸው ውጤታማ እያደረጋቸዉ እንደሆነም በጉራጌ ዞን የጉመር ወረዳ የበሽመንዳ እርሻ ልማት ባለቤት አቶ ሀሺም ጀማል ገለጹ፡፡

ጥር 09/2015 ዓ.ም

የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራ ትኩረት አድርገዉ በመስራታቸው ውጤታማ እያደረጋቸዉ እንደሆነም በጉራጌ ዞን የጉመር ወረዳ የበሽመንዳ እርሻ ልማት ባለቤት አቶ ሀሺም ጀማል ገለጹ፡፡

እርሻ ልማቱ ወተት እያመረተ ለአረቅጥ ከተማና የአካባቢው ህብረተሰብ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

የበሽመንዳ እርሻ ልማት ምርጥ ዘር ስንዴ በስፋት በማምረት ለደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በማቅረብ ፣ ድንች፣ በቆሎ እንዲሁም የፕሪምና የፖም ፍራፍሬ በስፋት እያለማ ይገኛል።

አርሶአደሩ ከእርሻ ልማቱ ተሞክሮ በመውሰድ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸዉ እንስሳትና የፍራፍሬ ምርቶች በስፋት በመዉሰድ የበለጠ ተጠቃሚነቱን ሊያረጋግጥ ይገባል።

የበሽመንዳ የግብርና ልማት ድርጅት ባለቤት አቶ ሀሺም ጀማል እንዳሉት የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራ ላይ ትኩረት አድርገው በመስራታቸው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸዉ እያረጋገጡ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ምርጥ ዘር ስንዴ በስፋት በማምረት ለደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት የሚያስረክቡ ሲሆን ድንች፣ በቆሎና በተጨማሪም የፕሪምና የፖም ፍራፍሬ በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም የተሻሻለ ዝርያ ያላቸውን እንስሳት ከብት፣ በግና ፍየል በማርባት የሚታወቁ ሲሆን በተለይ በድርጅቱ የሚመረተው ወተት ለአረቅጥ ከተማና በዙሪያው ለሚገኙ የአካባቢው ህብረተሰብ ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

አርሶአደሩ ከበሽመንዳ የተቀናጀ የግብርና ልማት ድርጅት ተሞክሮ በመውሰድ ጠንክሮ መስራት ቢችል ድህነትን በአጭር ጊዜ መቅረፍ እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

ከአዲስ አበባ መጥተው ከበሽመንዳ እርሻ ልማት ድርጅት የፕሪም ፍራፍሬ ከማሳ ገዝተው ሲለቅሙ ያገኘናቸው የአትክልትና ፍራፍሬ ነጋዴዎች አቶ አብረሃም ገብሩና አቶ ሰፋ ኢብራሂም በሰጡት አስተያየት አርሶ አደሩ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ሌሎች የግብራና ልማት ስራዎች ጠንክሮ ማምረት ቢችል ያለምንም ውጣ ውረድ ነጋዴው ማሳው ድረስ ገብቶ በመግዛት ተጠቃሚ መሆን ይችላል ብለዋል፡፡

የፖምና የፕሪም ፍራፍሬዎች ልማት በአካባበው አርሶ አደሮች ዘንድ የተለመዱ አለመሆናቸውን ተናግረው ከበሽመንዳ የግብርና ልማት ድርጅት ልምድ በመውሰድ ማልማት ቢችሉ አርሶ አደሩ በጣም ተጠቃሚ እንደሚያደረግ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡፡

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *