የተሻሻሉ የሰብልና የጓሮ አትክልት ምርጥ ዘሮች ለአርሶአደሩ የማቅረብ ስራ እየሰራ መሆኑም የአድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አስታወቀ።

ጳጉሜ 3/2014 ዓ. ም

የተሻሻሉ የሰብልና የጓሮ አትክልት ምርጥ ዘሮች ለአርሶአደሩ የማቅረብ ስራ እየሰራ መሆኑም የአድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አስታወቀ።

ዩኒየኑ ከ1 መቶ 34 ሺህ 9 መቶ በላይ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለ11 ወረዳዎች አሰራጭቷል።

የአድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን የግብአት ክፍል ኃላፊ ወይዘሮ ዚያዳ አብድላ እንዳሉት ዩኒየኑ ዘርፈ በዙ ስራዎች እየሰራ ነዉ።

የአድማስ ዩኒየን ህብረት ስራ ካስገነባቸዉ ትልልቅ ፋብሪካዎች መካከል ቸምና የኑግ ዘይት ፋብሪካና የቡና ማበጠሪያ ፋብሪካዎች ተጠቃሾች ናቸዉ።

ፋብሪካዉ የኑሮ ዉድነትን ለማረጋጋት የተለያዩ ምርቶች ከአምራች አርሶአደሮች በመሰብሰብ ለሸማች የህብረተሰብ ክፍሎች እያቀረበ እንደሆነም ተናግረዋል።

ምርታማነትን የሚያሳድጉ የተለያዩ የኬሚካል ፣ የእርሻ መሳሪያ አቅርቦት ፣ የተሻሻሉ የጓሮ አትክልት ምርጥ ዘሮች ከተለያዩ አስመጪ ድርጅቶች ጋር በመሆን ለአርሶአደሩ በሰፊዉ ለአርሶአደሩ የማቅረብ ስራ እየተሰራ መሆኑ አስታዉቀዋል።

በዩኒየኑ ስር የሚገኙ ከ2 መቶ በላይ መሰረታዊ የአፈር ማዳበሪያ የሚሰራጭባቸዉ ማህበራት በ11 ወረዳዎች ላይ የአፈር ማዳበሪያ አባል ለሆኑትም ላልሆኑትም ህብረት ስራ ማህበራቶች ስርጭት እንደሚካሄድም አብራርተዋል።

የተለያዩ የሰብል ምርጥ ዘሮች በቆሎ ፣ ቦለቄ ፣ስንዴ ፣ኑግ ፣ገብስና የተሻሻሉ ምርጥ ዘሮችን ከአስመጪዎችና ከአምራቾች እየተቀበለ እንደየወረዳዉ ተጨባጭ ሁኔታ የተለያዩ ዘሮችን ያቀርባል ብለዋል።

በኬሚካል አቅርቦት ዘርፍ የአረም መከላከያ ፣የተለያዩ የተባይ መከላከያዎች ከዉጭ ወደ ሀገር ዉስጥ ከሚያስገቡ ድርጅቶች ዉል በመግባት የማሰራጨት ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

ወደፊት የጓሮ አትክልቶች ፣ ኬሚካሎችና ሌሎችም ለአርሶአደሩ የሚጠቅሙ ግብአቶች ከዉጭ ለማስገባት ዉል ዝግጅት እየጨረሱ እንደሆነም አስታዉሰዋል።

የኬሚካል መርጫ ፣ የአትክልት ዉሃ ማጠጫ ፣ዜሮ ፍላይና ፊክስ ባግ የተሻሻሉ የእህል መያዣ ከረጢት ተባይን መከላከል የሚያስችሉ ሲሆን በ2014 አመተ ምህረት 25 ሺህ ለማሰራጨት እቅድ ተይዞ ፍተኛ እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበረም አስታዉሰዉ በዚህም 85 በመቶ ማሳካት እንደተቻለም አብራርተዋል።

የተለያዩ አርሶአደሩ የሚጠቀማቸዉ የእርሻ መሳሪያዎች በብዛት በማስመጣት ለአርሶአደሩ የማሰራጨት ስራ ሲሰሩም እንደነበር ተናግረዋል።

የአፈር መዳበሪያ በዘንድሮ አመት 196 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶአደሩ ለማሰራጨት እቅድ ይዘዉ እንደነበረም ተናግረዉ ከዚህ ዉስጥ 134 ሺህ 9 መቶ 88 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለ11 ወረዳዎች ስርጭት መካሄዱም ጠቁመዋል።

የአፈር ማዳበሪያ ከሌላዉ ጊዜ አንጻር በጣም ከፍተኛ የዋጋ ንረት ገጥሟቸዉ እንደነበረና በሚፈለገው ልክ ለአርሶአደሩ ተደራሽ ማድረግ እንዳልተቻለም አስታዉሰዋል።

የተሻሻሉ የበቆሎ ምርጥ ዘር ለማቅረብ በሰፊዉ አቅደዉ ሲሰሩበት እንደነበረም ተናግረዉ የሊሙ ሾኔዳሞት የሚባሉ ፓይነር የሚያደርጉ የበቆሎ ምርጥ ዘሮች ወደ ኦሮሚያ ክልሎችና በሌሎች አካባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት በቂ የበቆሎ ምርጥ ዘር ማቅረብ እንዳልተቻለም አስታዉሰዋል።

ቢኤች 546 የበቆሎ ምርጥ ዘር ከደቡብ ምርጥ ዘርና ከኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት በማስመጣት ለአበሽጌ፣ ለቀቤናና ለሌሎችም ወረዳዎች የማሰራጨት ስራ መስራቱም ተናግረዋል።

ጤፍ ስንዴ ፣ ቦለቄ ፣ ኑግ ፣ገብስና ሌሎችም ምርጥ ዘሮች ከተለያዩ የምርጥ ዘር ድርጅት በማስመጣት ለአርሶአየሩ እንደየፍላጎቱ ለማሰራጨት ተሞክሯል ብለዋል።

ለማህበረሰቡ የዘይት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በስፋት እየተሰራ ነው ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ
ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *