የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ፣በማሻሻልና በማላመድ ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞን እውን ለማድረግ እየሰራ መሆኑ የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ገለፀ።

በመሀከለኛ ደረጃ የሠለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ፣ በማሻሻልና በማላመድ ምርትንና ምርታማነትን በማሳደግ ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞን እውን ለማድረግ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ድርሻ የላቀ መሆኑን መምሪያው ገልፀዋል።

መምሪያ በ2014 ዓመተ ምህረት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከተውጣጡ ኃላፊዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ ዛሬ ውይይት አካሂዷል ።

የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈቱ አብዶ በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት የሠለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ፣በማሻሻልና በማላመድ ምርትንና ምርታማነትን በማሳደግ ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞን እውን ለማድረግ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ድርሻ የላቀ ነው።

በተለይም ወጣቱን በተለያዩ ስልጠናዎች ብቁ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣የስራ አጥ ቁጥር በመቀነስ እንዲሁም ወጣቱ በሀገራችን ሁለንትናዊ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ የማይተካ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በትኩረት ሊሠሩ ይገባል ብለዋል።

ገበያ ተኮር የሆኑ በጥናት የተረጋገጡና በትክክል የህበረተሠባችን ችግር የሚቀርፉ አጫጭርና መደበኛ ስልጠናዎችን በመስጠት ምርታማነትን ለማሳደግ ሀሉም ኮሌጆች በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በማህበረሰባችን ውስጥ የሚገኙ ሀገር በቀል ዕውቀቶችና የተፈጥሮ ሀብቶች በቴክኖሎጂ በመታገዝ አሰራራቸውን በማዘመን ህብረተሰቡን የበለጠ ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ ስራዎች በሁሉም ኮሌጆች በትኩረት እንደሚሠራም ገልፀዋል ።

በዞኑ በጣም ጥሩ አፈፃፀም ያላቸው በክልሉ ተወዳዳሪ የሆኑ ፖሊቴክኒክና እንደስትሪያል ኮሌጆች እንዳሉ የተናገሩት አቶ ፈቱ ሁሉም ኮሌጆች የተሻለና ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖራቸው የእርስ በርስና ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር የበለጠ የማጠናከር ሰራ መስራት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

በተመሣሣይ በቀጣይ አራት አመታት ካሉ ሁለት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አንዱን ወደ ዩኒሸርሲቲ ደረጃ ለማሳደግና አራት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እንዲኖሩ ግብ ተጥሎ እየተሠራ ነው ብለው ለዚህ ግብ መሳካት ሁሉም ኮሌጆች በተገቢ አቅደው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሠጡት አስተያየት እንደተናገሩት በ6 ወሩ አፈፃፀም የታዩ ጉድለቶች ከኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ምዘና ፣ቴክኖሎጂን ከማሸጋገር ፣ሞዴል ኢንተር ፕራይዞችን ከመፍጠርና መሠል በኮሌጆች በራሳቸው መፍታት የሚችሏቸውን ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ እንደ ዞን ከዚህ የተሻለ አፈፃፀም እንዲመዘገብና ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ የጋራ ርብርብ እደሚያደርጉም ገልፀዋል።

የኢንዱስትሪ ኤክሰቴንሽን መሠረት በማድረግ ሠልጣኙ ተመዝኖ ብቃቱ በማረጋገጥ ከስራ ጋር በማስተሳስር ጥራት
ያለው ምርትና አገልግሎት መስጠት የሚችል የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩም ተናግረዋል ።

በየደረጃው በሚገኙ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ተጥለው የሚገኙ ተሸክርካሪዎች፣ማሽኖችና ሌሎች ቁሳቁሶችን በኮሌጆች ደረጃ ቴክኖሎጂን ለማፍለቅ ፣ለማሻሻል እንዲሁም ለሠልጣኞች ተግባር ተኮር ስልጠና ለመሥጠት የሚረዱ ግብዓቶች እንዲያገኙ ቢደረግ ለስራቸው አጋዥ እንሚሆንም ጠቁመዋል።

በመድረኩ የመምሪያውና የመንግስት ኮሌጆች የ2014 ዓመተ ምህረት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የቀጣይ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *